የኖርዌይ መንግሥትና ኤርትራውያን ተገን ጠያቂዎች
ሐሙስ፣ ግንቦት 27 2007ማስታወቂያ
የኖርዌይ መንግሥት ኖርዌይ የሚገኙ ኤርትራውያን ተገን ጠያቂዎችን ባጋመስነው በጎርጎሮሳዊው 2015 ወደ ሃገራቸው ለማባረር በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታወቀ ። መንግሥት ይህን እርምጃ የሚወስደው የብዙ ኤርትራውያን ስደት ምክንያት መሆኑ የሚነገረውን የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ዘመን የኤርትራ መንግሥት ያሳጥራል በሚል እምነት መሆኑን ገልጿል ። ጥያቄአቸው ተቀባይነት ያላገኘ ተገን ጠያቂዎች ወደ ኤርትራ የሚመለሱበትን መንገድ ለማመቻቸትም የኖርዌይ መንግስት ባለሥልጣናት ወደ ኤርትራ እንደሚጓዙ ተገልጿል ። ይህን የኖርዌይ እርምጃ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ተቃውመዋል ።የስቶክሆልሙ ወኪላችን ቴድሮስ ምህረቱ ዝርዝሩን ልኮልናል
ቴድሮስ ምህረቱ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ