ሙዚቃ
የአሊ ቢራ እና የአሊ ሸቦ የሙዚቃ አስተዋፅዖ
እሑድ፣ ሐምሌ 7 2011
ማስታወቂያ
ባለፈው ሳምንት የድሬዳዋ እና የሐረማያ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት የሰጧቸው አሊ ቢራ እና አሊ ሸቦ በኢትዮጵያ መዚቃ በተለይ በኦሮሚኛ ሙዚቃ ከፍ ያለ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ናቸው። ሁለቱ የሙዚቃ ባለሙያዎች በኦሮሞ ሙዚቃ ከፍ ያለ ቦታ ላይ የሚቀመጠው የአፍረንቀሎ ባንድ አባላት ነበሩ። ከ57 አመታት በፊት ሁለቱን አሊዎች ጨምሮ በተለያዩ የሙዚቃ ባለሙያዎች የተመሰረተው አፍረንቀሎ ባንድ የኦሮሞን ፖለቲካ፣ ባህል እና ቋንቋ ለማሳደግ ከፍ ያለ ሚና እንደተጫወተ ይነገርለታል። በዛሬው የመዝናኛ መሰናዶ መሳይ ተክሉ አንድ ባለሙያ ስለሁለቱ አሊዎች አነጋግሯል።
መሳይ ተክሉ
እሸቴ በቀለ