1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራዉ ክልል ቀዉስ ጥላ ያጠላበት የ 2016 ዘመን መለወጫ

ሰኞ፣ ጳጉሜን 6 2015

በኢትዮጵያውያን ዘንድ በድምቀት የሚከበረዉ የዘመን መለወጫ ዋዜማ በአማራ ክልል ቀዝቃዛ እንደሆነ ተመለከተ። በክልሉ በሚታየዉ የሰላም እጦት ምንክንያት የአዲስ ዓመት አቀባበል እና አከባበሩ ላይ ጥላ እንደጣለበት በደብረማርቆስ፣ በደብረታቦር፣ በፍኖተ ሰላም፣ በደንበጫ፣ በፈረስ ቤት፣ በለሚ፣ በደሴና በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ገለፁ።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቸና ነዋሪ፣ አርሶ አደሩም ሆነ የእንስሳት ነጋዴው የደህንነት ስጋት ስላደረበት እንስሳቱን ወደ ገበያ ማውጣት አልቻለም ሲሉ ተናግረዋል።
የምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቸና ነዋሪ፣ አርሶ አደሩም ሆነ የእንስሳት ነጋዴው የደህንነት ስጋት ስላደረበት እንስሳቱን ወደ ገበያ ማውጣት አልቻለም ሲሉ ተናግረዋል።ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በአማራ ክልል በሚታየዉ የሰላም እጦት ምንክንያት የአዲስ ዓመት አቀባበልና አከባበሩ ላይ ጥላ እንደጣለበት በደብረማርቆስ፣ በደብረታቦር፣ በፍኖተ ሰላም፣ በደንበጫ፣ በፈረስ ቤት፣ በለሚ፣ በደሴና በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ገለፁ

This browser does not support the audio element.

በኢትዮጵያውያን ዘንድ በድምቀት የሚከበረዉ የዘመን መለወጫ እና ዋዜማዉ በአማራ ክልል ቀዝቃዛ እንደሆነ ተመለከተ። በአማራ ክልል በሚታየዉ የሰላም እጦት ምንክንያት የአዲስ ዓመት አቀባበል እና አከባበሩ ላይ ጥላ እንደጣለበት በደብረማርቆስ፣ በደብረታቦር፣ በፍኖተ ሰላም፣ በደንበጫ፣ በፈረስ ቤት፣ በለሚ፣  በደሴና በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ገለፁ። በዓሉ የአዲስ ተስፋ ምኞት የሚገለጥበት ቢሆንም የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በመዘጋታቸው ከጓደኞቻቻቸው የመልካም ምኞት መቀበልም፣ መላክም እንዳልቻሉም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።  አማራ ክልል አንፃራዊ ሠላም ሠፍኗል-ርዕሰ መስተዳድር
በደቡብ ጎንደር ዞን አንድ የደብረታቦር ከተማ ነዋሪ በዓሉን በተመለከተ የተለየ ነገር በከተማው አይታይም ብለዋል፣ የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት በመቋረጡም የመልካም ምኞት መልዕክቶችን መለዋወጥ አልቻልንም ሲሉ አክለዋል፡፡ አካባቢው እንስሳት የሚደልቡበት አካባቢ መሆኑን የነገሩን በምዕራብ ጎጃም ዞን የደንበጫ ከተማ ነዋሪ በነበረው አለመረጋጋት እንስሳት መድለብ አልቻሉም፣ ከሌላ ቦታ ሄዶ የእርድ እንስሳትንም መግዛት አልተቻለም፣ በመሀኑም አጋጣሚው በአዲሱ ዓመት አቀባበል ላይ አሉታዊ ጫና ፈጥሯል ነው ያሉት፡፡ የአማራ ክልል ውጊያ ወቅታዊ መረጃ
ሌላ የዚሁ ከተማ ነዋሪም የዓመት በዓሉን መድረስ የሚያመላክቱ ሙዚቃዎች አይሰሙም፣ ለእርድ እንስሳት የተዘጋጄ ሰው አላየሁም ሲሉ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በነበሩ የበዓል ዝግጅቶች የእርድ እንስሳትን ቀደም ብለው ይገዙ እንደነበር የነገሩን የምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቸና ነዋሪ፣ አርሶ አደሩም ሆነ የእንስሳት ነጋዴው የደህንነት ስጋት ስላደረበት እንስሳቱን ወደ ገበያ ማውጣት አልቻለም ብለዋል፡፡ በጦርነት ቆፈን ሆኖ በዓል ማክበር እንደማይቻል ደግሞ በምስራቅ ጎጃም ዞን የደብረማርቆስ ነዋሪው ይናገራሉ፡፡ 
በቅርቡ ብርቱ ውጊያ በነበረባት የፈረስ ቤት ከተማ ሁሉም ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ወደ ሥራ ባለመግባታቸው በአዲሱ ዓመት አከባበር ላይ ከፍተኛ ጫና እንደተፈጠረበት አንድ አስተያየት ሰጪ አስረድተዋል፡፡ በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ የተሸለ የእንስሳት አቅርቦት ቢኖርም የፍይል ዋጋ በእጅጉ በማደጉ ህብረተሰቡ ወደ ቅርጫ መዞሩ ተነግሯል፣ ሆኖም ወቅታዊ ሁኔታው በበዓሉ ድምቀት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን አንድ የከተማው ነዋሪ ተናግረዋል፡፡ በባሕር ዳር ከተማም የዓመት በዓል ድባቡ ብዙ ባይታይም የእንስሳት አቅርቦት መኖሩን ለማየት ችለናል፣ አስተያት ሰጪዎቹ እንደሚሉት ካለፈው ዓመት ሲነፃፀር የዋጋ መጨመር ይታያል ብለዋል፡፡ የፌደራል እና ክልል ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ 53 ግለሰቦች አዋሽ አርባ መታሰራቸውን ኢሰመኮ አረጋገጠ።
በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ ሰሞኑን በዋለው ገበያ የእንስሳቱም ሆነ ሌሎች ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ ሸቀጦች ዋጋ እጅግ ማሻቀቡን አንድ የከተማዋ ነዋሪ አመልክተዋል፣ ምክንያት ያሉት ደግሞ ወደ ከተማዋ የሚያስገቡ መንገዶች በሙሉ ባለመከፈታቸው ሸቀጦች እንደልብ እየገቡ ባለመሆናቸው ነው፡፡ ጦርነት የነበረባቸውን አብዛኛዎቹን የክልሉ አካባቢዎች መንግስት መቆጣጠሩን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ፣ ቢያሳውቁም በአንዳንድ የወረዳ አካባቢዎች ግጭቶች አሁንም እንዳሉ ደግሞ የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ይገልፃሉ፡፡ 
 በአማራ ክልል ግጭት ከተፈጠረበት ሐምሌ 2015 ዓ ም ጀምሮ በክልሉ 183 ሰዎች መገደላቸውንና ከ1000 በላይ የሚሆኑት ደግሞ መታሰራቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከሁለት ሳምንታት በፊት መግለፁ ይታወሳል፡፡ 

የምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቸና ነዋሪ፣ አርሶ አደሩም ሆነ የእንስሳት ነጋዴው የደህንነት ስጋት ስላደረበት እንስሳቱን ወደ ገበያ ማውጣት አልቻለም ሲሉ ተናግረዋል።ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ዓለምነው መኮንን


አዜብ ታደሰ 
ታምራት ዲንሳ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW