1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የአማራ ብድርና ተቋም በህወሓት ተዘረፈ መባሉ

ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 2 2013

የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) 90 ያህል ጽ/ቤቶቹ በህወሓት እንደተዘረፉበትና እንደወደሙበት ዐስታወቀ። ዝርፊያና ውድመቱ በርካታ የተቋሙን ደንበኛ አርሶ አደሮች ወደ ድህነት እንደሚመራ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አመለክቷል፣ አብቁተ ለመከላከያ ሠራዊቱ ማጠናከሪያ 80 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

CEO Bahir Dar   Mekonnen Yelewumwossen
ምስል DW/A.Mekonnen

ቡድኑ 2 ሚሊዮን ብር ከእየጽ/ቤቱ ዘርፎ መውሰዱ ተገልጧል

This browser does not support the audio element.

የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በዋናነት ለአርሶ አደሩ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት በመስጠት 25 ዓመታትን አስቆጥሯል። በቅርቡ የህወሓት ኃይሎች በአማራ ክልል በወረሯቸው አካባቢዎች 90 ጽ/ቤቶቹ በከፍተኛ ደረጃ መዘረፋቸውንና መውደማቸውን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መኮንን የለውምወሰን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።ውጊያው ወደ አማራ ክልል እየተጠጋ በሚመጣበት ወቅት 300 ሚሊዮን ብር ማሸሻቸውን የተናገሩት አቶ መኮንን ለእለታዊ ሥራ ማስኬጃ የነበረ 2 ሚሊዮን ብር ግን ቡድኑ ከእየጽ/ቤቱ ዘርፎ መውሰዱን አቶ መኮንን ይገልፃሉ። በጽ/ቤቶቹ ላይ የተፈፀመው ዝርፊያና ውድመት በርካታ አርሶ አደሮችን ወደ ድህነት እንደሚገፋውና በግብርነው ኢኮኖሚ ላይ ጫና እንደሚፈጥር ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፦ የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ጦርነቱን በግንባር እየመከተ ለሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ሚሊሻ፣ ፋኖና ሌሎች አጋር ኃይሎች ማጠናከሪያ ከሠራተኛውና ከተቋሙ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል። የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በ1988 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን በሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች በ472 ጽ/ቤቶችና 12ሺህ 600 ሠራተኞቹ እየታገዘ በገጠርና በከተማ የብድርና ቁጠባ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ነው። 

ዓለምነው መኮንን 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW