የአማራ ክልል አመራር በአሜሪካ
ረቡዕ፣ ኅዳር 26 2011ማስታወቂያ
በአማራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራ የልዑካን ቡድን ዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኙ የአማራ ተወላጆች እና ደጋፊዎቻቸው ጋር ካለፈው እሁድ ጀምሮ ውይይት እያካሄደ ነው። ባለፈው እሁድ በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው ውይይት ላይ የአማራ ክልል ተወላጆች በትምህርት በጤና በምህንድስና በኢንቬስትመንት እና በሌሎችም መስኮች ሀገራቸውን እንዲረዱ ጥሪ ቀርቦላቸዋል። ውይይቱ በሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ ከተሞችም ይቀጥላል። የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን ውይይቱን የተከታተሉ የዩናይትድ ስቴትስ ነዋሪዎችንም አስተያየት ያካተተ ዘገባ ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ