1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ክልል መንግሥት መግለጫና የተፈናቃዮች ጥሪ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 8 2013

የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እየወሰደ ባለው ማጥቃት የህወሓት ወራሪ ያላቸውን ኃይሎች ከአማራ ክልል እያስወጣ እንደሆነ የክልሉ መንግስት አስታወቀ፣ የህወሓት ወረራ በአማራ ክልል ተወስኖ ስላማይቀር የሌሎች ክልሎች ኃይሎችም የህለውነ ዘመቻውን እየተቀላቀሉ መሆኑን ክልላዊ መንግስት አመልክተል።

Äthiopien | Gizachew Muluneh
ምስል Alemenew Mekonnen/DW

የተፈናቃዮች ጥሪ

This browser does not support the audio element.

ከትናንት ጀምሮ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እየወሰደ ባለው ማጥቃት የህወሓት ወራሪ ያላቸውን ኃይሎች ከአማራ ክልል እያስወጣ እንደሆነ የክልሉ መንግስት አስታወቀ፣ የህወሓት ወረራ በአማራ ክልል ተወስኖ ስላማይቀር የሌሎች ክልሎች ኃይሎችም የህለውነ ዘመቻውን እየተቀላቀሉ መሆኑን ክልላዊ መንግስት አመልክተል። በሌላ በኩል በጦርነቱ ከተለያዩ ቦታዎች ተፈናቅለዉ ቆቦ የሚገኙ ነዋሪዎች ርዳታን እየጠየቁ ነዉ።  

የአማራ ክልላዊ መንግስት የህወሓት ኃይሎች በሰሜናዊ የአማራ አካባቢዎች ወረራ ፈፅሟል በሚል ሰሞኑን ያወጣውን የክተት ጥሪ ተቀብለው በርካቶች በትግሉ ለመሳተፍ ፍላጎት እያሳዩ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

እንደዚሁም የአማራ ልዩ ኃይልና ሌሎችም የፀጥታ አካላት የተሰጣቸውን የመልሶ ማጥቃት ትዕዛዝ ተግባራዊ በማድረግ እየተወሰደ ባለው እርምጃ ተወርረው የነበሩ አካባቢዎችን መልሶ እየተቆጣጠረ እንደሆነ የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን የመንግስት ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡

የህወሓት ጥቃት በአማራ ክልል ተወሰኖ እንደማይቀርና ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንደሚሰራ በዓለምአቀፍ ሚዲያዎች ጭምር ያረጋገጠው ነው ያሉት አቶ ግዛቸው ይህን ሴራ ለመበጣጠስ ሌሎች ክልሎችም የፀጥታ ኃይሎቻቸውን ወደ አማራ ክልል እላኩ እንደሆነ አስረድተዋል፣ እስካሁንም ኦሮሚያና ሲዳማ ክልሎች ልዩ ኃሎቻቸውን ልከዋልም ብለዋል፡፡

አሜሪካና አንዳንድ የአውሮፓ አገራት ሕወሓት በማይካድራ በቅርቡ ደግሞ በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ግድያና ማፈናቀል ሲደርስ አንድም ቃል ሳናገሩ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ግን ተገቢ እንዳልሆነ አስረድተዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ተፈናቅለው በቆቦ የሚገኙ ወገኖች ችግር ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

አንድ የራያ አማራየወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አመራር ለዶቼ ቬለ እንዳሉት ተፈማቃዮች በየዘመዱተጠግተው እንደሚገኙና አሁን እርዳታ ለማቅረብ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አስቸጋሪ ነው ብለዋል፡፡

 

ዓለምነዉ መኮንን

ሸዋዩ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW