1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ክልል ርምጃና መግለጫ

ረቡዕ፣ ግንቦት 24 2014

የክልሉ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ግዛቸዉ ሙሉነሕ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት መንግሥታቸዉ ፋኖን በተለይ የሚያሳድድበት ምክንያት የለም።ይሁንና አቶ ግዛቸዉ አክለዉ እንዳሉት ማንም ሰዉ በጥፋት ሲጠረጠር በሕግ ይጠየቃል።

Äthiopien | Gizachew Muluneh
ምስል Alemenew Mekonnen/DW

«የአማራ ክልል ፋኖን አያሳድድም፤ ተጠርጣሪን ግን ያስራል» ግዛቸዉ ሙሉነሕ

This browser does not support the audio element.

 የአማራ ክልል መንግሥት ፋኖ ተብሎ የሚጠራዉን ታጣቂ ኃይል  ነጥሎ የሚከታተልበት ምክንያት እንደሌለዉ አስታወቀ።የክልሉ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ግዛቸዉ ሙሉነሕ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት መንግሥታቸዉ ፋኖን በተለይ የሚያሳድድበት ምክንያት የለም።ይሁንና አቶ ግዛቸዉ አክለዉ እንዳሉት ማንም ሰዉ በጥፋት ሲጠረጠር በሕግ ይጠየቃል።በአማራ ክልል ሰሞኑን 4500 የሚደርሱ የመንግሥት የፀጥታ ኃይል ባልደረቦች፣ የፋኖ ታጣቂዎች፣ ጋዜጠኞችና የመገናኛ ዘዴ ባለሙያዎች ታስረዋል።አቶ ግዛቸዉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የታሰሩት ሰዎች «የክልሉን ሰላም ለማደፍረስ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ» ተብለዉ የተጠረጠሩ ናቸዉ።የባሕርዳሩ ወኪላችን ዓለምነዉ መኮንን ያነጋገራቸዉ አንድ የፀጥታ ባለሙያ በበኩላቸዉ አንድ ሐገር ዉስጥ ሁለት የታጠቀ ኃይል ሊኖር አይችልም ይላሉ።የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ዛሬ የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ባለፉት ጥቂት ቀናት ከውስጥና ከውጪ በመቀናጀት የክልሉን ሰላም ለማደፍረስ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ ያሏቸው በርካታ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡
“መንግሥት የተለያዩ ወንጀሎችን የፈፀሙ ተጠርጣሪዎችን ይዣለሁ ቢልም መንግሥት ግን ያነጣጠረው ከፋኖ ላይ ነው ይባላል እንዴት ያዩታል? ” ተብለው የተጠየቁት አቶ ግዛቸው “ፋኖን በተለየ ሁኔታ አናሳድድም፣ በወንጀል ሲጠረጠር ደግሞ ማንም ቢሆን ፋኖም ፣ ጳጳስም፣ ሸክም ፕረዚደንትም ከተጠረጠረ ይጠየቃል” ብለዋል::ኢ-መደበኛ አደረጃጀት ስድብ ማለት አይደለም ያሉት አቶ ግዛቸው ይህን አደረጃጀት መልክ የማስያዝ ስራ የሚሰራ ይሆናል ሲሉ በመግለጫቸው አመልክተዋል፡፡በክልሉ የፀጥታ ሥራ ላይ ሰፊ ልምድ ያላቸውና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዲግሪያቸውን በግጭትና ኮሙዩኒኬሽን ላይ እየሰሩ ት አቶ አየለ አናውጤ መንግሥት እያደረገ ያለውን የህግ ማስከበር ሥራ በአዎንታዊ መንገድ እንደሚመለከቱት ገልጠዋል፡፡
በአንድ ክልል ሁለት የታጠቀ ኃይል መኖር እንደሌለበት ያነሱት አቶ አየለ በተለያየ አደረጃጀት የነበሩና በመንግሥት ስር ለመታቀፍ ፍላጎት ያላቸው ከመንግሥት ውጪ ያሉ አደረጃጀቶች አባላት በመንግሥት ሥር መሆን አለባቸውም ብለዋል፣ ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለስ የሚፈልጉም ወደ ሥራቸው፣ ሥራ የሌላቸውን ደግሞ መንግሥት በተለያዩ ሥራዎች ማደራጀት እንደሚኖርበትም አስረድተዋል፡፡በቁጥጥር ስር የሆኑ ተጠርጣሪዎች በወቅቱ ለምን ፍርድ ቤት አልቀረቡም ተብለው የተጠየቁት የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ግዛቸው ብዙዎቹ እየቀረቡ መሆናቸውን ጠቁመው በሚቻለው ፍጥነት ይሰራል ነው ያሉት፡፤ የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በቅርቡ በሰጠው መግለጫ ከ4ሺህ 500 በላይ ተጠርጣሪዎችን መያዙንና ከዚህ ውስጥ 1ሺህ 780 ያህል በመንግሥት የፀጥታ መዋቅር ውስጥ ያሉ ናቸው ማለቱ ይታወሳል፡፡

 

ዓለምነዉ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW