1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ክልል ሾፌሮች ሮሮ 

ሰኞ፣ የካቲት 7 2014

አንድ ሾፌር እንዳሉት ከአዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል ጎሐፅዮን በኩል ወደ አማራ ክልልና ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ መሄድ ፈተና ሆኗል፡፡ ከጎንደር ወደ ገንዳ ውሀ ለ6 ዓመታት በሾፌርነት የሰሩት ሌላ የከባድ ጭነት መኪና አሽከርካሪ በዚሁ መስመር በኦሮሚያ ክልል በኩል ባለው የአባይ ሸለቆ በአንድ ዓመት ብቻ 10 አሽከርካሪዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል ብለዋል፣

Äthiopien LKW-Fahrer Protest in Dire Dawa
ምስል M.Teklu/DW

አሽከርካሪዎች በጉዞ ላይ ድብደባ ግድያ እና ብዙ ችግር እየገጠማቸው ነዉ

This browser does not support the audio element.

በአማራና በኦሮምያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ጥቃቶች እየተፈፀሙባቸው በመሆኑ ሥራቸውን በአግባቡ መስራት እንዳልቻሉ የከባድ ጭነት መኪና ሾፌሮች ተናጋሩ። 10 ሾፌሮች በስራ ላይ ሳሉመገደላቸውን ከ100 በላይ ሥራቸውን መተዋቸውን ሾፌሮቹ ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ይሁንና  መንግስት በአማራ ክልል የሚፈፀሙ ጥቃቶችን በተቀናጀ መልኩ እየተከላከልሁ ነው ይላል፡፡ 
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች በአሽከርካሪዎች ላይ ግድያን ጨምሮ፣ መታገት መደብደብና መሰል ጥቃቶች እየተፈፀሙ እንደሆኑ ነው አሽከርካሪዎች ለዶይቼ ቬሌ የተናገሩት፡፡ ቅሬታቸውን ካሰሙት መካከል አቶ ሰጡ ብርሀን እንዳሉት ከአዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል ጎሐፅዮን በኩል ወደ አማራ ክልልና ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ መሄድ ፈተና ሆኗል፡፡ ከጎንደር ወደ ገንዳ ውሀ ለ6 ዓመታት በሾፌርነት የሰሩት አንድ ከባድ ጭነት መኪና አሽከርካሪ ተመሳሳይ ጥቃቶች እየደረሱ መሆናቸውን አስረድተዋል።  በዚሁ መስመር በኦሮሚያ ክልል በኩል ባለው የአባይ ሸለቆ በአንድ ዓመት ብቻ 10 አሽከርካሪዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል ብለዋል፣ ምናልባት ጥቃቱ እልባት ቶሎ ካልተሰጠው አሽከርካሪዎች የራሳቸውን እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ እንግዳው ጠገናው፣ ከአሽከርካሪዎች ጋር በተያያዘ በአማራ ክልል ያለውን ችግር ለማስወገድ በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ አንዳንድ የፀጥታ አካላት ለታጣቂው መረጃ ይሰጣሉ ተብሎ ለተነሳው ቅሬታም ዳይሬክተሩ ከጠላት ጋር ተቀናጅተው የሚሰሩ ጥቂት ኃይሎች ስለሚኖሩ የማጥራት ስራ እየተሰራ ነው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ 


ዓለምነው መኮንን 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW