1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ክልል የሠላም ምክር ቤት የተደራደሩ ጥሪ

ሐሙስ፣ መስከረም 30 2017

በአማራ ክልል ያለው ጦርነት በሰላምና በድርድር እንዲቋጭ የክልሉ የሰላም ምክር ቤት ዳግም ጠየቀ። ምክር ቤቱ ሁለቱም ኃይሎች የህብረተሰቡ ስቃይና እንግልት እንዲያበቃ ለድርድር ቅድሚያ እንዲሰጡ ጠይቋል ። የሰላም ጥረቱ አሁንም እንዳልተሟጠጠ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ያየህይራድ በለጠ ለዶይቼ ቬሌ ገልጸዋል፡፡

Äthiopien | Amhara Friedensrat
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የአማራ ክልል የሰላም ምክር ቤት ለተፋላሚዎች የሰላም ጥሪ አቀረበ

This browser does not support the audio element.

የአማራ ክልል የሠላም ምክርቤት ጥሪ

በአማራ ክልል ያለው ጦርነት በሰላምና በድርድር እንዲቋጭ የክልሉ የሰላም ምክር ቤት ዳግም ጠየቀ፣ ምክር ቤቱ ሁለቱም ኃይሎች የህብረተሰቡ ስቃይና እንግልት እንዲያበቃ ለድርድር ቅድሚያ እንዲሰጡ ጠይቋል፣ የሰላም ጥረቱ አሁንም እንዳልተሟጠጠ ነው የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ያየህይራድ በለጠ ለዶይቼ ቬሌ የተናገሩት፡፡

በአማራ ክልል የቀጠለው ጦርነት

በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች አሁንም ጦርነቶች እየተካሄዱ እንደሆነ ነዋሪዎች እየገለፁ ነው፣ ባለፈው ሳምንት በተለይም በምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች ከባድ ውጊያዎች በፋኖ ታጣቂዎችና በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች መካከል ሲካሄዱ መሰንበታቸውን ነዋሪዎቹ ሰሞኑን ለዶይቼ ቬሌ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

እንደነዋሪዎቹ ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተሰላም፣ ደንበጫ፣ ጂጋ፣ ፈረስቤትና በምስራቅ ጎጃም ዞን አማኑኤልና አካባቢው ጦርነቶች ሲካሄዱ ሰንብተዋል፡፡

ጦርነት ዘላቂ ሠላም አያመጣም።

አንዳንድ የፋኖ አመራሮች ከመንግሥት ጋር ለመወያየት አወንታዊ ምላሽ ሰጡ መባሉ

ሰሞኑን መንግስት በሰጠው መግለጫ በክልሉ ያለውን ጦርነት ለማስወገድ የተጠናከረ እርምጃ እንደሚወስድ አመልክቷል፡፡

የአማራ ክልል የሰላም ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ያየህይራድ በለጠ ግን ሰላም በጦርነት ሊመጣ እንደማይችል ነው የተናገሩት፡፡

“የሰላም በር ምንጊዜም ዝግ አይሆንም፣ በእርግጥ ሰላም በአንድ ቀን አይመጣም፣ ብዙ ጥረቶች ይጠይቃል፣ በጦርነትም ዘላቂ  ሰላም አይገኝም፣ ሰላም የሚመጣው በውይይትና በድርድር ብቻ ነው” ብለዋል፡፡

የሰላም ተስፋ፣ስጋቱና እንቅፋቱ

መንግስት በሙሉ ኃይሉ “ህግማስከበር” ያለውን እርምጃ እንደሚወስድ ባለፈው ሳምንት በሰጠው መግለጫ አመልክቷል፣ መግለጫውን የሰጡት  የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊና የመከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ናቸው፡፡

መንግስት በሙሉ ኃይሉ “ህግማስከበር” ያለውን እርምጃ እንደሚወስድ ባለፈው ሳምንት በሰጠው መግለጫ አመልክቷል፣ መግለጫውን የሰጡት  የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊና የመከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ናቸው፡ምስል Alemnew Mekonnen/DW

መንግስት የተጠናከረ ህግ የማስከበር እርማጃ እወስዳለሁ ማለቱ

የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መንገሻ በመግለጫቸው በተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎች መደረጋቸውን አንስተዋል፣የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ጭምር ጥረት ማድረጋቸውን ያስታወሱት ዶ/ር መንገሻ፣ መንግስትም በማነኛውም ሰዓትና ቦታ ለሰላም ዝግጁ እንደነበር ጠቅሰዋል፣ ሆኖም የሰላም ጥሪውን ታጣቂዎቹ ባለመቀበላቸው መንግስት ወደ ተግባራዊ እርምጃ ገብቷል ነው ያሉት፡፡

በአማራ ክልል የታወጀው የ10 ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቆይታ ተጠናቆ ይሆን?

የመከላከያ ሰራዊት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ በበኩላቸው የሰላም ትሪ ለበርካታ ጊዜ ቢደረግም ተግባራዊ ምላሽ ባለመገኘቱ ሁከትንና ብጥብጥን ለማስወገድና የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል፡፡

 ታዲያ ይህ የሰላም በሮች መሟጠጣቸውን የሚያሳይ እንደሆነ አድርገው የሚናገሩ ሰዎች ይደመጣሉ፣ አቶ ያየህይራድ ግን በዚህ አይስማሙም፡፡

የሰላም በሮች መሟጠጣቸውን የሚያሳይ እንደሆነ አድርገው የሚናገሩ ሰዎች ይደመጣሉ፣ አቶ ያየህይራድ ግን በዚህ አይስማሙም፡፡ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የሠላም በሮች ተሟጥጠው አልተዘጉም መባሉ   

እንደ አቶ ያየህይራድ ሁለቱም ባለስልጣኖች የተናገሩት “ሰላም ተሟጥጧል” ማለት እንደማያስብልና የሰላም ጥረቱ ግን አሁንም እንደሚቀትል ገልጠዋል፡፡

አቶ ያየህይራድ ሁለቱ አካላት ወደ ድርድር እንዲመጡ በርካታ ጥረቶች መካሄዳቸውን ጠቅሰው አሁንም ጥረቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን፣ ታዋቂ ግለሰቦችንና ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ጭምር በመጠቀም ሁለቱ ኃይሎች ወደ ውይይትና ድርድር እንዲመጡ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡ የፋኖ ታጣቂዎችና የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች አሁንም ለውይይትና ለድርድር ዝግጁ እንዲሆኑም አቶ ያየህይራድ በድጋሜ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአማራ ክልል የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና አንድምታው

ሁለቱም ኃይሎች ለድርድር አዎንታዊ ምላሽ ስለመስጠታቸው

አቶ ያየህይራድ ከዚህ በፊት ለዶይቼ ቬሌ እንደተናገሩት፣ በተደራጀ ሁኔታ በአንድ ሆነው ባይመጡም በተናጠል የአገኟቸው የፋኖ አመራሮች ለመደራደር አወንታዊ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ “ በተናጠል ደረጃ ድርድሩን የሚደግፉ አሉ፣ ይህንን ደግሞ በተጠናከረ መንገድ እንቀጥልበታለን” ነው ያሉት፡፡

ምስል Alemnew Mekonnen/DW

አቶ ያየህይራድ፣ ፋኖ ወደ አንድነት ይመጣል የሚል እምነት አላቸው፣ ታታቂ ቡድኑ አንድ ሆኖ መግለጫ እንደሚሰጥ የሚያምኑ አመራሮች መኖራቸውን ጠቅሰው ምክር ቤቱም ይህ እንዲሆን እንደሚሰራ ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡

«ሀገራዊው ውይይት ከታቀደው ጊዜ ተገፍቶ ሊጀመር ይችላል» የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን

እስካሁን የአማራ ክልል መንግስት መልካም ምላሽ እንደሰጠ ሰብሳቢው አመልክተው፣ በፌደራል ደረጃም ከሰላም ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተደርጓል ብለዋል፣ ለምክር ቤቱም አስፈላጊው ድጋፍ ይደረግለታል መባላቸውን አስረድተዋል፣ የሰላም ምክር ቤቱን ጥረትም የሰላም ሚኒስቴር እንደሚደግፈው እንደተገለፀላቸውም አብራርተዋል፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ጋር ለመወያየትም ቀጠሮ እንዲያዝላቸው እንደጠየቁና ምላሽ እየጠበቁ እንደሆነ ገልጠዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW