የአማራ ክልል የብሔራዊ ምክክር ተሳታፊዎች አጀንዳዎቻቸውን ለኮሚሽኑ አስረከቡ
ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 4 2017
ሠሞኑን በክልሉ ሲካሄድ የነበርው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደትና በአዲስ አበባ ለሚካሄደው አገር አቀፍ ጉባኤ የሚሳተፉ ተወካዮችም ተመርጠዋል፡፡ ከአዊ ብሔረስብ አስተዳደር ተወክለው የመጡ አንድ አስተያየት ሰጪ ሁሉም ሀሳቡን አውጥቶ መስጠቱን ጠቁመው የተነሱ ሀሳቦች በመንግሥት ተቀባይነት ካላቸው ውጤት ያመጣሉ የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በብሔራዊ ምክክር እንዲሳተፉ ተጨማሪ ጥሪ ቀረበ
ሌላው አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው የማያግባቡን ነገሮች መፍትሔ አግኝተው ተግባብተን መኖር የሚያስችል ውይይት ማድረግ እንደተቻለ ነው ለዶይቼ ቬሌ አስተያየታቸውን የሰጡት፡፡
አዲስ አበባ ላይ በሚደረገው አገራዊ ምክክርም የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የተሻለ መግባባት እንደሚፈጠር ገልጠዋል፡፡
በመነጋገር የማይፈታ ችግር እንደሌለ የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ በሂደቱም የተሻለ ነገር ይመጣል ብለዋል፡፡ የምክክር መድረኩ ሲጠናቀቅ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮንሚሽን ኮሚሽነር መላኩ ወልደማሪያም በአማራ ክልል የተካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብና በአዲስ አበባ ጉባኤ የሚወከሉ ተሳታፊዎችን የመምረጡ ሂደት በስኬት መጠናቀቁን ገልጠዋል።
በአማራ ክልል ከመጋቢት 27 እስከ ሚያዘያ 4/2017 ዓም የተካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው ጉባኤ የሚሳተፉ ተወካዮች ተመርጠዋል፡፡ በሁለት ምዕራፍ ሲካሄድ በቆየው የአማራ ክልል የምክክር ሂደት ከ6ሺህ በላይ ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡
ዓለምነው መኮንን
እሸቴ በቀለ