የአማራ ክልል ግጭት፣ የመኪኖች መቃጠልና የመንገድ መዘጋት
ማክሰኞ፣ የካቲት 25 2017
ከቀናት በፊት ሰሊጥ ጭነው ከጎንደር ወደ ባህርዳር ሲያመሩ የነበሩ ሰድሰት ተሳቢ መኪኖች በሊቦ ከምከም ወረዳ ጣራ ገዳም ቀበሌ አዲስ ዘመን ከተማ አቅራቢያ መቃጠላቸውን ኑሪዎች ተናገሩ መኪኖቹ ታጂበው እየተጉዙም ነበር ብለዋል
«የተቃጠለዉ ስድስት መኪና ነዉ ሰሊጥ የጫነ ማለት ነዉ ታጂቦ ሲመጣ ከስድስቱ አንዱ ሲመታ ተቃጠለ ከዚያ ሌሎቹም ተቃጠሉ»
በአካባቢው ከዚህ ቀደም በመኪኖች ላይ ዝርፊያ ይፈጸም ነበር ያሉን ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአካባቢው ኑሪም እንደዚህ ግን የከፋ አልነበረም ይላሉ
«ያዉ ብዙ ጊዜ መንገድ ላይ ጫካ ስለሆነ ቦበታዉ መኪኖች ላይ ዝርፊያ ነበረ እስካሁን ድረስ መኪና ተቃጥሎ አያዉቅም አሁንላይም ተቃጠሉና የተወሰኑ መኪኖች ወደዚህ ወደ አዲስ ዘመን መጥተዋል»
መኪኖቹ የተቃጠሉት ለዝርፊያ አይደለም የሚሉት ሌላ አስተያየት ሰጭም ጉዳዩ ከኮቴ ክፍያ ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ ይናገራሉ
«ይህ ዝርፊያ አይመስለኝም ለመንግስት እጀባ እየከፈሉ ነዉ ለምን ለኛ አይከፍሉም ይመስለኛል የኮቴ ቀረፅ አለ አይደለ መኪኖች ባለሀብቶች ከፍለዉ ነዉ የሚታጀቡት ለመንግስት ለምን ለኛ አይከፍሉም እንጂ ሌላ ነገር ዘረፋ አይመስለኝም»
በቃጠሎው የወደመው ንብረት በርካታ ነው የሚሉት አንድ አሽከርካሪም ስድስት መኪኖች የጫኑት ሰሊጥ መቃጠሉን ይገልጻሉ
«ስድስት መኪና ተቃጥሉል አንድ መኪና ወድቋል ሰሊጥ ነዉ ኤክስፖርት በአንድ መኪና ላይ በአማካኝ380 ኩንታል አንድ መኪና ይይዛል አንድ ኩንታል 23ሺህ ብር ነዉ አባዛዉ መኪናዉ አንዱ ከ15 ሚልየን ብር በላይ ነዉ የሰዉ ህይወት አለ የታገቱ ሹፌሮች አሉ ይሄን ያክል ነዉ»
በአማራ ክልል በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪና ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ ታጣቂዎች በመኪኖች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተናግረዋል
«ከ16 ያላነሱ የጭነት መኪናዎች ከጎንደር ወደ ባህርዳር አቅጣጫ ሲመጡ የሊቦ ከምከም ወረዳ ደቡብ ጎንደር ጣራ ገዳም ደፋጦ ቆይቶ ጥይት በመተኮስ ከጫኑት ተቀጣጣይና በሙቀት በቀላሉ ሊቃጠል የሚችል ሰሊጥ ምርት በአብሪ ጥይት በሙምታት ንበብረቱ እንዲወድም አድርጎል»
ይህ በእንዲህ እንዳለምበደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በጸጥታ ችግር ምክንያት ከዞኑ ዋና ከተማ ደሴ ጋር የሚያገናኝው መንገድ መዘጋት ለከፋ ማህበራዊ ቀውስ መዳረጉን ኑሪዎች ተናግረዋል
«ከቁንዲ ጀምረዉ ኩታበር መናህሪያ ድረስ በእግራቸዉ ይሄዳሉከዚያ በኃላ ነዉ ደሴ በሚኒባስ የሚገቡት ገንዘባቸዉም የደርሶ መልስ እጥፍነዉ የሚኩፍሉት መኪናዉ በባዶ ስለሚመለስ(ህብረተሰቡም ሉችግር እየተጋለጠ ነዉ በዚህ በሰላም ችግር ነዉ የሚሉት ታገትን ምግብ ወደዚህ እንዳይመጣ ህብረተሰቡ በጣም እንግልት ላይ ነዉ ያለዉ»
የመንገድ መዘጋቱ የምግብ ሸቀጦችን ለወረዳው ኑሪ በአግባቡ እንዳይደርስ መሰናክል መሆኑን ኑሪዎች ሲናገሩ የወረዳው አስተዳዳሪር አቶ ጌጢ ደረስ ግን በጸጥታው ችግር ምክንያት መንገድ መዘጋቱ በአካባቢው ኑሮ ውድነት አስከትላል ይላሉ
«ኑሮ ማረጋጋት የሚቻለዉን ሁሉ እየተደረገ ነዉ መንገዱ ከፀጥታ አኻያ ሲቆም ነጋዴዎችም ሸቀጥ ያለማግኘት እዚህም ያለዊን በአግባቡ ስራ ላይ ያለማዋል ችግር ስለሚያጋጥምችግር ነበር ከዚህ ዉጭ ክልሉ ያለበት ነባራዊ ሁኔታ ጦርነት ሌሎች ተጓዳኝ ችግሮች ስለሚያመጣ የእኛንም አካባቢ የጎበኙ ናቸዉ»
ኢሳያስ ገላዉ
ነጋሽ መሐመድ
ታምራት ዲንሳ