1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ክልል ፀጥታና ኢንተርኔት

ሐሙስ፣ ሐምሌ 27 2015

ዛሬ እስከ ማርፈጃዉ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብ ምስራቅ ጎጃም ዉስጥ በተለያዩ ከተሞችና አካባቢዎች የተኩስ ልዉዉጥ ሲደረግ ነበር

Äthiopien | Yilkal Kefale
ምስል Alemenew Mekonnen/DW

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥሪ ካለፈዉ የተለየ አይደለም

This browser does not support the audio element.

 

አማራ ክልል በሸመቀዉ  ፋኖ በተሰኘዉ ታጣቂ ኃይልና በኢትዮጵያ መንግስት ፀጥታ አስከባሪዎች መካከል በየአካባቢዉ የሚደረገዉ ግጭትና የተኩስ ልዉዉጥ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።የባሕር ዳሩ ወኪላችን ዓለም መኮንን የየአካባቢዉን ነዋሪዎችን ጠቅሶ እንደነገረን ዛሬ እስከ ማርፈጃዉ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብ ምስራቅ ጎጃም ዉስጥ በተለያዩ ከተሞችና አካባቢዎች የተኩስ ልዉዉጥ ሲደረግ ነበር።በተኩስ ልዉዉጥ ስለደረሰ ጉዳት የተነገረ ነገር የለም።የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ወደ ጎንደርና ወደ ላሊበላ የሚያደርገዉን በረራ ማቋረጡን አስታዉቋል።ከትናንት ማታ ጀምሮ በአማራ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት ተዘግቷል።

ዓለምነዉ መኮንን 

ነጋሽ መሐመድ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW