የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ከመንግስት ጋር «አልተደራደርኩም» አለ (የታረመ)
ሐሙስ፣ ጥር 22 2017
ማስታወቂያ
የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር አልተደራደርኩም አለ።አቶ እስክንድር ነጋ የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት በዉጪ ሸምጋዮች አማካይነት ከመንግሥት ጋር ድርድር ጀምሯል የሚሉ ዘገቦች ሰሞኑን ተሰራጭተዉ ነበር።የድርጅቱ መሪ እስክንድር ነጋ ዛሬ እንዳሉት ግን ድርጅታዉ ድርድር አልጀመረም።ይሁንና የድርጅቱ መሪዎች ሥለ ድርጅቱ ዓላማ፣ በአማራ ክልል ይፈፃማሉ ሥለሚባሉ የጦር ወንጀሎችና ሥለ ሠብአዊ ርዳታ አቅርቦት ከዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ተወካዮች ጋር መወያየታቸዉን አቶ እስክንድር አስታዉቀዋል።
ነጋሽ መሐመድ
ፀሐይ ጫኔ