1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካኑ ባለስልጣን የአፍሪቃ ጉብኝት

ዓርብ፣ ኅዳር 29 2010

የአሜሪካን የዉጭ ጉዳይ መ/ቤት የአፍሪቃ ጉዳዮች ምክትል ተጠባባቂ ሚኒሥትር ዶናልድ ያማማቶ በሦስት የአፍሪቃ ሃገራት ጉብኝታቸዉን እያካሄዱ ነዉ። በመቃዲሹ ሶማሊያ ተገኝተዉ የሀገሪቱን የፀጥታ ጉዳይ ጉባኤ ተካፍለዋል። ዛሬም አዲስ አበባ ላይ ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር መነጋገራቸዉን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

Donald Yamamoto (L)
ምስል picture-alliance/dpa/J. L. Scalzo

በምግብ ዋስትና እና በሰላም ማስከበር ጉዳይ ይነጋገራሉ፤

This browser does not support the audio element.

በዛሬዉ ዕለትም አዲስ አበባ ላይ ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር መነጋገራቸዉን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የአሜሪካዉ ባለስልጣን ከዚህም ሌላ በኢትዮጵያ ቆይታቸዉ ከአፍሪቃ ኅብረት ባለስልጣናትም ጋር በምግብ ዋስትና እና በሰላም ማስከበር ጉዳዮች ላይ እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ አንድ የኢትዮጵያ የቀድሞ ዲፕሎማት በግብፅ እና ኢትዮጵያ ጉዳይ፤ እንዲሁም ኢራን በአካባቢዉስላላት ተጽዕኖም ሊነጋገሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። ከዋሽንግተን ዲሲ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ተጨማሪ ዘገባ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW