የአሜሪካን የምርጫ ዘመቻ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 18 2013![US Wahlkampf Tour Joe Biden Kamala Harris](https://static.dw.com/image/55409950_800.webp)
ማስታወቂያ
በመጪው ሳምንት ማክሰኞ የሚካሄደው የአሜሪካን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፉክክር፣ ከሁለቱም ፓርቲዎች ጋር ባልወገኑ ወሳኝና ጥቂት ግዛቶች ላይ አትኩሯል። በነዚሁ ግዛቶችና በአጠቃላይ በሐገራዊ ቅድሚያ ትንበያ የዴሞክራቶቹ እጩ ተወዳዳሪ ጆ ባይደን እየመሩ ነው። ያም ከአራት ዓመት በፊት የተወዳደሩት የቀድሞ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን እየመሩ ቆይተው የገጠማቸውን ዓይነት አስገራሚ ሽንፈት ላለመጎናጸፍ ዴሞክራቶች ያለ ዕረፍት ዘመቻቸውን ተያይዘውታል። ለተወሰነ ጊዜ በሥራ ምክንያት መዘገብ አቋርጦ የነበረው አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
አበበ ፈለቀ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ