1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካዉ የዉጭ ጉዳይ ሚ/ር ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነዉ

ሐሙስ፣ የካቲት 30 2015

የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር አንቶኒዮ ብሊንከን በቅርቡ "በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል" ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ጉብኝቱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማጠናከር እድል የሚሰጥ ነው ያሉት የሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ባለስልጣኑ መቼ እንደሚመጡ ግን አልገለፁም።

Äthiopien Ambassdor Meles Alem
ምስል Solmon Muche/DW

የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መርመራ እንዲቋረጥ ስለቀረበዉ ጥያቄ "ከአጋሮቻችን ጋር እየተነጋገርንበት ነው"

This browser does not support the audio element.


የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን በቅርቡ "በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል" ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ጉብኝቱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማጠናከር እድል የሚሰጥ ነው ያሉት የሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ባለስልጣኑ መቼ እንደሚመጡ ግን አልገለፁም። 
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መርማሪ ቡድን የጀመረው ሥራ እንዲቋረጥ ያቀረበችውን ጥያቄን በተመለከተ እና ይህንን ጥያቃ የመብት ተሟጋቾች መቃወማቸውን በተመለከተ የተጠየቁት አምባሳደር መለስ "ከአጋሮቻችን ጋር እየተነጋገርንበት ነው" ብለዋል። 
የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰሞኑን የተሳሳተ እና ተቀባይነት የሌለው መግለጫ አውጥተዋል ያሉት ቃል ዐቀባዩ ኢትዮጵያ ይህንን የግብጽን አቋም "ኋላ ቀር" ብለውታል። 
በመንግሥት በኩል በተካሃዱ ወቅታዊ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ ያተኮረው የዛሬው መግለጫ
የኢትዮጵያ መንግሥት ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ ገንቢ የተባለ የዲፕሎማሲ ሂደት ላይ መሆኗን ተገልጿል።
ቃል ዐቀባዩ ተጠይቀው ምላሽ ከሰጡባቸው ጉዳዮች መካከል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያ ጉብኝት ይገኝበታል። "አንቶኒ ብሊንከን በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በጉብኝታቸው ከአገራችን ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይነጋገራሉተናግረዋል።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መርማሪ ቡድን ሥራ እንዲቋረጥ ያቀረበችው አቤቱታ ከዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ተቃውሞ ገጥሞታልና የመንግሥትን አቋም ቢገልፁልን የተባሉት አምባሳደር መለስ አለም  "ከአጋሮቻችን ጋር እየተነጋገርንበት ነው" ብለዋል።
የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ እየሄደችበት ያለው አካሄድ አደገኛ መሆኑን ጠቅሰው ከሰሞኑ መግለጫ ማውጣታቸው መንግሥትን እንዳሳዘነም ተናግረዋል። "መግለጫ ለማውጣት የሚያስገድድ ምንም አዲስ ነገር አልተፈጠረም" ብለዋል። ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ስላለችበት ወቅታዊ የግንኙነት ደረጃም ተጠይቀው ነበር።
"ኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል ያለው ግንኙነት ምንም ውጥረት የለም። በጣም የተሻለ የግንኙነት ደረጃ ላይ ነው ያለው" ብለዋል። ችግርን ሽሽት ኢትዮጵያ ውስጥ የገቡ 100 ሺህ የሱማሌላንድ ስደተኞች ድጋፍ ተደርጎላቸው ይቆያሉ ያሉት ቃል ዐቀባዩ የኢትዮጵያ መንግሥት ዜጎችን ለስደት የዳረገው ችግር በሰላም እንዲፈታ ሲጠይቅ መቆየቱንም ተናግረዋል።

ሰለሞን ሙጬ 
አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW