1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካው ልዑክ በመቐለው ዝግ ስብሰባ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 29 2015

በፕሪቶሪያው ውል መሰረት የእስካሁኑ አፈፃፀም እና ሌሎች ጉዳዮችብ በተመለከተ የአሜሪካ የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ ልኡክ አምባሳደር ማይክ ሐመር እና ሌሎች የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች ከትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር መሪዎች ጋር በትላንትናው ዕለት በመቐለ ከተማ ተወያይተዋል።

USA/Äthiopien Mike Hammer US-Sonderbeauftragter am Horn von Afrika
ምስል Seyoum Getu/DW

ውይይቱ ለመገናኛ አውታሮች ዝግ ነበር ተብሏል

This browser does not support the audio element.

በፕሪቶሪያው ውል መሰረት የእስካሁኑ አፈፃፀም እና ሌሎች ጉዳዮችብ በተመለከተ የአሜሪካ የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ ልኡክ አምባሳደር ማይክ ሐመር እና ሌሎች የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች ከትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር መሪዎች ጋር በትላንትናው ዕለት በመቐለ ከተማ ተወያይተዋል። ለመገናኛ አውታሮች ዝግ ነበር በተባለው ውይይት የውጭ ያሏቸው ኃይሎች ከትግራይ ክልል ስለሚወጡበት፣ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው ስለሚመለሱበት፣ በክልሉ ስለተቋረጠው ሰብአዊ ርዳታ ቀጣይነት እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች መነሳቱም በትግራይ ክልል ባለስልጣናት በኩል ተነግሯል። 

ለሚድያዎች ዝግ በነበረው በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እና በማይክ ሐመር በተመራው የአሜሪካ መንግስት ልኡክ ውይይት ዙርያ፥ ከውይይቱ በኋላ ለጋዜጠኞች ማብራርያ የሰጡት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ሴክሬታሪያት አቶ አማኑኤል አሰፋ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህወሓት ሕጋዊ ሰውነት ዙርያ በቅርቡ ያስተላለፈው ውሳኔም በውይይቱ መነሳቱ የጠቆሙ ሲሆን፥ የቦርዱ ውሳኔ በሰላም ስምምነቱ ላይ አሉታዊ ጫና እንደሚፈጥር ለልኡኩ መገለፁ አንስተዋል። 

ሌላው በልኡኩ እና በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የነበረ የውይይት ነጥብ ለትግራይ የተቋረጠው ሰብአዊ እርዳታ ዙርያ ሲሆን፥ መሻሻሎች ከተደረጉ የአሜሪካ መንግስት የተቋረጠው የምግብ እርዳታ እንዲቀጥል ፍላጎት እንዳለው መንፀባረቁ ተነግሯል። 

ትላንት መቐለ ከመጡ የአሜሪካ መንግስት ልኡካን ውጭ ባለፉት ሳምንታት መቀመጫቸው አዲስ አበባ ያደረጉ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች እንዲሁም የዓለምአቀፉ ተቋማት ተወካዮች፣ የሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ለመገምገም እንዲሁም ከጦርነቱ በኃላ የሚጠበቀው ዳግም ግንባታ ዙርያ ለመምከር በትግራይ ጉብኝት ሲያደርጉ ሰንብተዋል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW