1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ ምርጫ ውጤት እና የአውሮጳ ምላሽ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 27 2017

ትናንት የተካሄደው የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ውጤት ይፋ መሆኑን ተከትሎ የተለያዩ ሃገራት መሪዎች ለተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ደስ ያልዎት መልእክታቸውን በመላክ ላይ ናቸው።

የአሜሪካ እና የአውሮጳ ኅብረት
የዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮጳ ኅብረት ሰንደቅ አላማዎች ፎቶ ከማኅደርምስል picture-alliance/dpa/J. Kalaene

የአሜሪካ ምርጫ ውጤት እና የአውሮጳ ምላሽ

This browser does not support the audio element.

 

 የአውሮጳ ሕብረት አባል ሃገራትም እንዲሁ በየበኩላቸው ከትራምፕ አስተዳደር ጋር ለመሥራት ዝግጁነታቸውን እየገለጹ ነው። ሮይተርስ እንደውም ከቀትር በፊት ባስተላለፈው ዜናው «ትራምፕ አሸንፌያለሁ ስላሉ፤ የዓለም ሃገራት መሪዎች እንኳን ደስ ያልዎት ለማለት እየተጣደፉ ነው» ሲል የመንግሥታቱን የደስታ መልእክት ወርፏል።

እስካሁን በይፋ ከታዩ የእንኳን ደስ ያልዎት መልእክቶች፤ ከአውሮጳ የጀርመን፤ የፈረንሳይ፤ የጣሊያን፤ የስፔን፤ የኔዘርላንድ፤ የሀንጋሪ፣ የዩክሬን፣ የፖላንድ፤ ሮማኒያ ይጠቀሳል። እስራኤል፣ ህንድ፣ ጃፓን፣ ስዊድን፤ ኖርዌይ፤ እንዲሁም ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳንም ትራምፕን እንኳን ደስ ያልዎት ብለዋል።

ከጀርመን የቀኝ ጽንፈኛው አማራጭ ለጀርመን ፓርቲ ተባባሪ መሪ አሊስ ቫይደል በበኩላቸው የትራምፕ ድል የጅምላ ስደትን አይሆንም የማለትና፤ የኤኮኖሚ ውድቀትን የሚቃወም ድምፅ ውጤት ነው ሲሉ በኤክስ ገጻቸው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።   

ትራምፕ ከዚህ ቀደም የአትላንቲክ ማዶ ግንኙነት ላይ ያስከተሉት አሉታዊ ተጽዕኖ፤ እንዲሁም የዩክሬን ሩሲያ ጦርነትን በሚመለከት ያላቸውን አቋም በማሰብ አብዛኛው የአውሮጳ መሪዎች የእሳቸው መመረጥ እንደሚያሰጋቸው ሲገልጹ ቆይተዋል። ዛሬ ስጋታቸው እውን ሆኗልና ብራስልስ ላይ ምን እየታሰበ ይሆን? ስንል እዚያ የሚገኝ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሤን በአጭሩ ሁኔታውን እንዲያስቃኘን ጠይቀናል።

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW