የአሜሪካ ሶማሊያውያን ስጋት
ዓርብ፣ መስከረም 17 2006ማስታወቂያ
በኬንያው የናይሮቢ ግዙፍ የገበያ ማዕከል ውስጥ አሸባብ የፈፀመው ጥቃት አሜሪካን ከሶማሊያና ከአሸባብ ጋር በተያያዘ የምታራምደውን የውጭ ፖሊሲ እንደገና እንድትመረምር ሳያደርጋት እንደማይቀር ተነገረ ። ጥቃቱ የአሜሪካንንና የኬንያን የፀጥታ ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠናክር ይጠበቃል ። በሌላ በኩል በዚሁ ጥቃት ሶማሊያውያን አሜሪካውያን ተሳትፈዋል መባሉ በአሜሪካ የሚገኙ ሶማሊያውያንን ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ከቷል ። አሜሪካን የሚገኙ ወደ አክራሪነት የተቀየሩ ሶማሊያውያንም አሜሪካን ውስጥ ጥቃት ሊፈጽሙ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ ። የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን በጉዳዩ ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ተንታኞችን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።
አበበ ፈለቀ
ሂሩት መለሰ