1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ በኤርትራ ጄነራል ላይ የጣለችዉ ማዕቀብ አንድምታ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 18 2013

ዩናይትድ ስቴትስ በኤርትራ የጦር ጄነራል ላይ ማዕቀብ መጣሏ የማስጠንቀቂያ ርምጃ ነው ሲሉ ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያ ገለፁ። የሕግ አዋቂና ጠበቃ ደረጀ ደምሴ እንዳሉት የኤርትራ መንግሥት በኤርትራ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዩሐንስ ላይ ማዕቀብ መጣሏ በሃገሪቷ ላይ ጫና ለማሳደር ያለመ የማስጠንቀቂያ ርምጃ ነው።

USA Rechtsanwalt Dereje Demsie aus Äthiopien
ምስል Tariku Hailu/DW

በኤርትራ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ጄነራል ላይ የተጣለው ማዕቀብ

This browser does not support the audio element.

ዩናይትድ ስቴትስ በኤርትራ የጦር ጄነራል ላይ ማዕቀብ መጣሏ የማስጠንቀቂያ ርምጃ ነው ሲሉ ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያ ገለፁ። የሕግ አዋቂና ጠበቃ ደረጀ ደምሴ እንዳሉት የኤርትራ መንግሥት በኤርትራ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዩሐንስ ላይ ማዕቀብ መጣሏ በሃገሪቷ ላይ ጫና ለማሳደር ያለመ የማስጠንቀቂያ ርምጃ ነው። በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የኤርትራን ወቅታዊ ኹኔታ በቅርበት የሚከታተሉት ዶክተር በርሔ ሐብተ ጊዮርጊስ በበኩላቸው የአሜሪካ አዲሱ የማዕቀብ ርምጃ የይስሙላ ነው በማለት አጣጥለውታል። ገንዘብ በዓለም ዙሪያ ለሌለው እና ለማያንቀሳቅስ ሰው ያን አይነት ማዕቀብ መጣል ቀልድ ነው ብለዋል። ታሪኩ ኃይሉ ከአትላንታ ጆርጂያ ተከታዩን ዘገባ አልኮልናል። 
ታሪኩ ኃይሉ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW