1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ የማዕቀብ እቅድ ሁለቱንም ሃገሮች ይጎዳል መባሉ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 4 2014

ዩናይትድስቴትስ በኢትዮጵያ ላይ የምጣኔ ሃብት ማዕቀብ ለመጣል እያጤነች መኾኗን ማስታወቋ የሁለቱን ሃገሮች ስትራቴጂካዊ ግንኙነትና ጠቀሜታ የሚጎዳ መሆኑን በአሜሪካ ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸው የሲቪክ ድርጅቶች ተወካዮች አስታወቁ።

Belgien US Präsident Joe Biden im Königlichem Palast von Brüssel
ምስል Patrick Semansky/AP Photo/picture alliance

ጫናዉን ለመከላከል ጠንካራ ዲኘሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ይካሄዳል

This browser does not support the audio element.

ዩናይትድስቴትስ በኢትዮጵያ ላይ የምጣኔ ሃብት ማዕቀብ ለመጣል እያጤነች መኾኗን ማስታወቋ የሁለቱን ሃገሮች ስትራቴጂካዊ ግንኙነትና ጠቀሜታ የሚጎዳ መሆኑን በአሜሪካ ዶይቸ ቨለ ያነጋገራቸው የሲቪክ ድርጅቶች ተወካዮች አስታወቁ። የአሜሪካ ኢትዮጵያውያን ሕዝብ ጉዳዮች አስፈፃሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ መስፍን ተገኑ እንደገለፁት የዩናይትድስቴትስ አካሄድ የሁለቱን ሃገሮች ወዳጅነትና ጥቅም የሚጎዳ ነው። የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ድምፅ ንቅናቄ ተወካይ ወይዘሮ ሜሮን አሐዱ በበኩላቸው የኢትዮጵያና አሜሪካን የጋራ ጥቅም ይጎዳል ያሉትን ጫና ለመከላከል የሚያስችል የተጠናከረ የሕዝብ ዲኘሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ይካሄዳል ብለዋል።

 

ታሪኩ ኃይሉ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW