1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ኅብረተ ሰብሰሜን አሜሪካ

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያሳለፈው ውሳኔ

ታሪኩ ኃይሉ
ረቡዕ፣ ሰኔ 24 2018

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመወለድ የሚገኝ ዜግነትን ለማስቀረት ያደረጉትን ሙከራ ውድቅ አደረገ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያዎች፣ የዚህ ውሳኔ ፋይዳ፣ ከፍተኛ መሆኑን እና ለኢትዮጵያውያንም በብዙ መልኩ አስተውጽኦ ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዋኅንግተን ዲሲ
የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዋኅንግተን ዲሲ ፎቶ ከማኅደር

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያሳለፈው ውሳኔ

This browser does not support the audio element.

 


ሰነድ አልባ ስደተኞች በአሜሪካ የሚወልዷቸው ልጆች የአሜሪካ ዜግነት እንዳያገኙ ለማገድ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ፕሬዚዳንታዊ ትዕዛዝ በማውጣት፣ መብቱን ለማስቀረት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል።
የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግን ትናንት ባስተላለፈው ውሳኔ፣ የትራምፕን ሀሳብ  6 ለ 3 በሆነ አብላጫ ድምፅ ቀልብሶታል። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን የተመለከተው፡ የፕሬዚዳንት ትራምፕን ማዘዣ የተቃወሙ ወላጆች እና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ባቀረቡት ክስ መነሻነት መሆኑን የሕግ ባለሙያው ዶክተር ፍጹም አቻምየለህ ለዶቼ ቨለ ገልጸዋል።


«ያንን ማዘዣ የሚቃወሙ ወላጆች እና የሰብአዊ ድርጅቶች ደግሞ ከሰሱ፤ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ ይሄ የፕሬዚዳንቱ ማዘዣ ከአሜሪካ ሕገ መንግሥት 14ተኛው አንቀጽ ጋር ይቃረናል ብሎ ወሰነ።የአሜሪካ ሕገ መንግሥት 14ተኛው ማሻሻያ አንቀጽ ማንም አሜሪካ የተወለደ ልጅ፣ ወላጆቹ ዜጋ ሆኑ አልሆኑ ፈቃድ ኖራቸው አልኖራቸው ዜጋ ነው የሚል ትእዛዝ ነው የወጣው።»

እስከ ሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዘለቀው በዚህ ጉዳይ፣ከዘጠኙ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የዕድሜ ዘመን ዳኞች አብላጫውን ቁጥር የያዙት፣150 ዓመት ያስቆጠረውን በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት እንዲቀለበስ አልፈቀዱም። በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡን ሌላው የሕግ ባለሙያ አቶ አሳምን መኮንን በበኩላቸው፣ ውሳኔው ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው እንደሆነ ይናገራሉ።

«አብዛኛዎቹ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች የወሰኑት ውሳኔ፣ አሜሪካ ውስጥ መወለድ ብቻ በቂ እንደሆነ ነገር ግን የሚወለዱት ልጆች እናት እና አባታቸው እዚህ ሀገር ወረቀት ይኑራቸው አይኑራቸው ፣የመኖሪያ ፈቃድ ይኑራቸው አይኑራቸው፣ ዜጋም ይሁኑ በመኖሪያ ፈቃድ ይኑሩ እሱ አይደለም፤ ዋናው ነገር እዚህ መወለድ ብቻ በቂ ነው የሚል በመወለድ የሚገኝ ዜግነት በሕገመንግሥቱ ሲሠራበት የነበረው ነገር ሕገ መንግሥታዊ ነው በዛ ነው መቀጠል ያለበት የሚል ውሳኔ ነው፥ በጣም ከፍተኛ የሆነ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ነው።»

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕፎቶ ከማኅደርምስል፦ Hu Yousong/Xinhua/picture alliance


የውሳኔው አንድምታ በተለይ ለኢትዮጵያኖች ምንድን ነው?


«ኢትዮጵያ ውያን እንግዲህ አሜሪካ ውስጥ ብዙ ኢዘጋ የሆኑ አሉ። ግሪን ካርድ ያላቸው አሉ። ወረቀትም የሌላቸው ኢትዮጵያውያን አሉ። እዚህ ሀገር በተለያየ ጊዜያዊ በሆነ ቪዛ የሚኖሩ ሰዎች አሉ።ዞሮ ዞሮ ወረቀት ያላቸውም የሌላቸውም የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸውም የሌላቸውም እዚህ ሀገር ልጆች ቢወልዱ ልጆቻቸው የአሜሪካ ዜግነት እያገኙ ይቀጥላሉ ማለት ነው።»'
በፕሬዚዳንቱ ትህዛዝ ምክንያት ቢያንስ ወደ 200 ሺህ የሚሆኑ ልጆችን ዜግነት የሚያሳጣ እንደነበር የተናገሩት ዶክተር ፍጹም፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለእነዚህ ወላጆች ትልቅ እፎይታን የፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል።


«ይህ ትእዛዝ ከወጣ በኋላ የተወለዱ ልጆች ዜግነት እንዲከለከሉ ነበር ያሰበው እሱ፤ ግን ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መከልከል የለባቸውም ብሎ ወሰነ። ስለዚህ አንድምታው፣ አሁን ለጊዜው እነዚህ 200 ሺህ የሚሆኑ ልጆች፣ ዜጎች ናቸው። ሁለተኛ የአሜሪካ የዛሬ 125 ዓመት የተጻፈው ሕገ መንግሥት ማሻሻያ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተቋጨ ማለት ነው። ከእዚህ በኋላ እየተነሳ እዚህ ሀገር የተወለዱ ልጆች ዜጎች አይደሉም ማለት አይቻልም። የአሜሪካን ሀገር የሕግ ሥርዓቱን አሁን እንዳየነው ፣r ሕገ መንግሥቱን የሚነካ ከሆነ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሕገ መንግሥቱን እና ማሻሻያዎቹን እንዳይነካ መስመር አሰመረ ማለት ነው።» ብለዋል።

ታሪኩ ኃይሉ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW