1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ ጫና በኢትዮጵያ 

ረቡዕ፣ ጥቅምት 3 2014

ዩናይትድ ስቴትስ በሰሜን ኢትዮጵያ ተባብሶ ለቀጠለው ግጭት መልስ ለመስጠት የምጣኔ ሐብት ማዕቀብን ጨምሮ አማራጮችን በማጤን ላይ መሆኗን ዐስታወቀች። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ኘራይስ ትናንት ለጋዜጠኞች እንደገለፁት አሜሪካ ለሰሜን ኢትዮጵያ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የተለያዩ አማራጮችን በማየት ላይ ነች።

USA Ned Price Sprecher des Außenministeriums
ምስል picture alliance / ASSOCIATED PRESS

አሜሪካ አማራጮችን በማጤን ላይ ናት

This browser does not support the audio element.

ዩናይትድ ስቴትስ በሰሜን ኢትዮጵያ ተባብሶ ለቀጠለው ግጭት መልስ ለመስጠት የምጣኔ ሐብት ማዕቀብን ጨምሮ አማራጮችን በማጤን ላይ መሆኗን ዐስታወቀች። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ኘራይስ ትናንት ለጋዜጠኞች እንደገለፁት አሜሪካ ለሰሜን ኢትዮጵያ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የተለያዩ አማራጮችን በማየት ላይ ነች። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከአፍሪቃ ኅብረትና አውሮጳ ባለሥልጣናት ጋር በኢትዮጵያ ጉዳይ ውይይት ማድረጋቸውም ተመልክቷል። ሃገራቱ በኢትዮጵያ ተፋላሚ ኃይላት በአፋጣን የተኩስ አቁም አድርገው ወደ ውይይት እንዲገቡ ሲሉም አሳስበዋል። 

ታሪኩ ኃይሉ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW