1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 3 2016

ፕሬዚደንት ጆሴፍ ባይደንና ቀዳማዊት እመቤት ዶክተር ጂል ባይደን፣በያዝነው ዓመት በጆርጂያ የምርጫ ዘመቻ አካሄደዋል። ተቀናቃኛቸው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ትናንት እዚህ ጆርጂያ ተገኝተው የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አካሄደዋል። አንድ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር እንደሚሉት፣ጆርጂያ በዘንድሮው ምርጫ ቁልፍ ሚና ትጫወታለች።

የአሜሪካን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪዎች ጆ ባይደንና ዶናልድ ትራምፕ
የአሜሪካን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪዎች ጆ ባይደንና ዶናልድ ትራምፕ ምስል imago images

የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ

This browser does not support the audio element.

የምርጫው ወሳኝ ግዛቶች

በአሜሪካ  ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ወቅት ዕጩዎቹ ከፍተኛ ድምጽ ባላቸው እንደ ካሊፎርኒያና ኒውዮርክን በመሳሰሉ ትልልቅ ግዛቶች ጊዜና ገንዘባቸው ሲያጠፉ አይስተዋሉም።ይልቁንም ጥቂት በሚባሉ ሞገደኛ ግዛቶች ላይ ተግተው የምርጫ ዘመቻ ያካኼዳሉ።  ውላቸው የማይታወቀው አሪዞና፣ዊስኮንሲን፣ሚችጋን፣ፔንሲልቫንያና ፍሎሪዳ ግዛቶች ወሳኝ ድምጽ አላቸው።ጆርጂያም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከነዚሁ ግዛቶች ጎራ ተቀላቅላለች።

የጆርጂያ ሚና

በኬኔሳው ስቴትስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር ኬርዌን ሳዊንት፣ እንደሚሉት፣ጆርጂያ በዘንድሮው ምርጫ ቁልፍ ሚና ትጫወታለች። እንደእርሳቸው ገለጻ፣ጆርጂያ ላይ ሳያሸንፉ የዘንድሮውን የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ማሸነፍ አይቻልም፤ያን ያህል አስፈላጊ ነው።" የምርጫ ባለሙያዎች እንደሚናገሩትም፣በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አብዛኛዎቹ መራጮች ድምጽ የሚሰጡትን ፓርቲ አይቀያይሩም።ቅድመ ምርጫ በአሜሪካ

 ነገር ግን 15 በመቶ ያህል የሚሆኑት፣በቅስቀሳ ዐሳባቸውን ሊቀይሩ የሚችሉ ናቸዉ ተበሎ ይታመናል። እነዚሁ መራጮች ወሳኝ በተባሉ ግዛቶች የሚኖሩ ናቸው። ፕሬዚደንት ጆሴፍ ባይደንና ቀዳማዊት እመቤት ዶክተር ጂል ባይደን፣በያዝነው ዓመት በጆርጂያ የምርጫ ዘመቻ አካሄደዋል።

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆባይደን ምስል Paul Morigi/Getty Images for Care Can't Wait Action

የትራምፕ ጉብኝት በጆርጂያ

ተቀናቃኛቸው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ትናንት እዚህ ጆርጂያ ተገኝተው የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አካሄደዋል። ትራምፕ በግዙፉ አርትስፊልድ ጃክሰን አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፣ በአውሮፕላን ጣቢያው የተገኙ ጥቂት ደጋፊዎቻቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል። የአሪዞና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጽንስ ማስወረድን አስመልክቶ፣ያሳለፈውን ውሳኔ ተመርኩዞ ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቀርቦላቸዋል ነበር። ፍርድ ቤቱ ጽንስ ማስወረድ የሚከለክል ህግ ነው ያጸደቀው። የፍርድ ቤቱ ውሳኔ እ.ኤ.አ በ1864 በጽንስ ማስወረድ ላይ የተላለፈው አጠቃላይ እገዳተፈጻሚ እንዲሆን ወስኗል። የቀድሞ ፕሬዝዳንት ለጋዜጠኞች በሰጡት ምላሽ የአሪዞና ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጽንስ ማቋረጥ ውሳኔ ላይ እጅግ እጅግ ርቀት ሄዷል፣ይስተካከላለል ብዬ አስባለኹ ብለዋል።የአሜሪካን የምርጫ ዘመቻና ወሳኝ ክፍለ ግዛቶች   

"እንደምታውቁት፣ሁሉም የግዛቶች መብት ነው።ያ ይስተካከላል ሃገረ ገዢው ወደ ምክንያታዊነት እንደሚመለሱት እርግጠኛ ነኝ።"ጽንስን ማስወረድ በተመለከተ የግዛቶቹ መብት እንደሆነም ትራምፕ ተናግረዋል። የፕሬዚዳንት ባይደን ቃል አቀባይ ማይክል ተይለር፣ትራምፕ በአሁኑ ጊዜ በአሪዞና ውስጥ እየተከሰተ ላለው መከራና ትርምስ ተጠያቂ አድርገዋቸዋል።

ዶናልድ ትራምፕምስል Joe Raedle/AFP/Getty Images

የስነ ተዋልዶ መብት

ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ በነገው ዕለት ወደአሪዞናዋ ቱክሰን ከተማ ለመጓዝ አቅደዋል። የጉዟቸው ዓላማ ለስነ ተዋልዶ ጤና መብት ለመታገል እንደሆነ ተመልክቷል። ባይደን ለሁለተኛ ዘመነ ስልጣን እወዳደራለሁ አሉየስነ ተዋልዶ መብቶች በዘንድሮው ምርጫ እንደስደተኞች ጉዳይ ሁሉ ትኩረት የተሰጠው አጀንዳ ሆኗል። በተመሳሳይ ሁኔታ የፍሎሪዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጽንስ ማስወረድን የሚመለከቱ ውሳኔዎች ላይ ገደብ መጣሉ ይታወቃል። ዶናልድ ትራምፕ የጆሴፍ ባይደን አስተዳደር እስራኤልን ቸል ብሏል በማለትም ወቀስዋል። የቀድሞ ፕሬዝዳንት፣ ለዴሞክራቶች ወይንም ለፕሬዚዳንት ጆሴፍ ባይደን  ድምጽ የሰጠ ማንኛውም አይሁዳዊ አዕምሮውን መመርመር አለበት ብለዋል። ትራምፕ ይህን ይበሉ እንጂ፣ባይደን የእስራኤልን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል። ቴህራን ሶሪያ በሚገኘው ቆንስላ የተገደሉባትን  አመራሮች ለመበቀል እርምጃ ልትወስድ ትችላለች የሚል ስጋት አይሏል።

ታሪኩ ኃይሉ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW