1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

ባይደን ለእስራኤልና ፍልስጤም የሁለት መንግሥት መፍትሔ ለማስገኘት እየሰሩ መሆናቸውን አስታወቁ

ሰኞ፣ ግንቦት 12 2016

ፕሬዚዳንቱ ትናንት ጠዋት አትላንታ በሚገኘው፣ሞርሐውስ ኮሌጅ የተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣በጋዛ እና በእስራኤል እየሆነ ያለው በጣም አሳዛኝና ልብ ሰባሪ እንደሆነ ገልጸዋል።

ባይደን በሙርሐውስ ኮሌጅ
ባይደን የእስራኤልና ሐማስ ጦርነትን አስመልክተው ሲናገሩ፣ በጋዛ እየሆነ ያለው ነገር በጣም አሳዛኝ እና ልብ ሰባሪ እንደሆነ በመግለጽ የተማሪዎቹን ስጋት ተጋርተዋል።ምስል፦ Alex Brandon/AP/picture alliance

ባይደን በሙርሐውስ ኮሌጅ ያደረጉት ንግግር

This browser does not support the audio element.

ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንስቶ፣በበርካታ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ፣በቀጠለው የእስራኤልና ሐማስ ጦርነት መነሻነት፣ተማሪዎቹ ለፍልስጤም ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ ሰልፎችን ሲያካሄዱ ሰንብተዋል።

ተማሪዎቹ፣ዩኒቨርሲቲና ኮሌጆቻቸው ከአስራኤል ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያቋርጡ፣ጦርነቱ የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ እያስከተለ በመሆኑም፣እስራኤል በሐማስ ታጣቂ ቡድን ላይ የምታደርገውን  ጥቃት በመቃወም፣ዋይት ሐውስ በገንዘብና በወታደራዊ ቁሳቁስ ለእስራኤል የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲቆም በመጠየቅ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ይህንን የፍልስጤም ደጋፊ ሰልፎች ተከትሎ፣ ፕሬዚዳንት ባይደን ትናንት በታዋቂው ሞርሐውስ  ኮሌጅ ባደረጉት ንግግር፣ከኮሌጁ ተማሪዎች ጋር ለመገናኘት ዕድሉን ተጠቅመውበታል።

ማሕደረ ዜና፣ የጋዛ ጦርነት እንዲቆም የሚጠይቁ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጥሪ

ባይደን የእስራኤልና ሐማስ ጦርነትን አስመልክተው ሲናገሩ፣ በጋዛ እየሆነ ያለው ነገር በጣም አሳዛኝ እና ልብ ሰባሪ እንደሆነ በመግለጽ የተማሪዎቹን ስጋት ተጋርተዋል።

"በጋዛ እና በእስራኤል እየሆነ ያለው ነገር በጣም አሳዛኝ ነው።ሐማስ በእስራኤል ላይ ተከታታይ ጥቃት በመፈጸም፣የንጹሐንን ህይወት እያጠፋ ሰዎችን አግቶ ይገኛል።"

ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ንግግራቸው፣ በረሃብ አፋፍ ላይ በምትገኝው እና የህክምና ቁሳቁሶች አቅርቦት በሚያስፈልጋት ጋዛ፣የሰብዓዊ ቀውስ ላይ አጽንኦት ሰጥተውታል።

በእስራኤልና ሐማስ ጦርነት አፋጣኝ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ጥሪ ያቀረቡት ሚስተር ባይደን፣ታግተው የተወሰዱት እስራኤላውያን ወደ ቤታቸው እንዲመለሱና ተጨማሪ ሰብዓዊ ዕርዳታ፣ በጦርነት ወደምትታመሰው ጋዛ እንዲገባ የሚያስችል ስምምነት ላይ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ባይደን በሙርሐውስ ኮሌጅ ንግግር ማድረጋቸውን የተቃወሙ ነበሩ ምስል፦ Patrick Semansky/AP/picture alliance

የሁለት መንግሥት መፍትሔ

ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኝ ይረዳ ዘንድ እየሰሩ ያሉትን ሲናገሩ የሚከተለውን ብለዋል።

" በመጨረሻ የሁለት መንግስት መፍትሄ እንድናገኝ እየሰራሁ ነው። ሁለቱ ህዝቦች በሰላም በደህንነት እና በክብር የሚኖሩበት ብቸኛ መፍትሄ።ይህ በዓለም ላይ ካሉት በጣም ከባድ እና ውስብስብ ችግሮች አንዱ ነው እና ምንም ቀላል ነገር የለም።ቤተሰቤን ጨምሮ ብዙዎቻችሁን እንደሚያናድድ እና እንደሚያስከፋ አውቃለኹ።ከሁሉም በላይ ግን፣ጉዳቱ ልባችኹን እንደሚሰብብራችኹ አውቃለኹ፤የእኔንም ይሰብራል።"

ለጥቁር አሜሪካውያን ስተላለፉት  መልዕክት

ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ባይደን ምርጫው በተቃረበበት ወቅት፣በሞርሐውስ ኮሌጅተገኝተው ንግግር ማድረጋቸው፣በጥቁር አሜሪካውያን ፊት ለመታየትና መልዕክት ለማስተላለፍም ዕድል አስገኝቶላቸዋል።

በባይደን ንግግር የእስራኤል እና የሐማስ ጦርነት ከፍ ያለ ቦታ አግኝቷልምስል፦ AFP/Getty Images

ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካኖች የምርጫ ዘመቻ

"ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በላይክብረወሰን በሆነ ቁጥር ጥቁር አሜሪካውያን ሥራና የጤና መድኅን አላቸው። ዲሞክራሲ ደግሞ መስማትና መደማመጥ ነው።የእናንተ ከመሣሪያ ጥቃት ነጻ የሆነ ማኀበረሰብ፣ ከአየር ንብረት ቀውስ የጸዳች ፕላኔት እንዲኖረው ይጠይቃለን።እናም ዓለምን የመለወጥ ኀይሉን ያሳያል።"

በምረቃ ስነስርዓት መድረኩ የታየው ተቃውሞ

ፕሬዚዳንቱ ንግግራቸውን ትከትሎ፣ከሞርሐውስ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተሰጥቷቸዋል።በዚሁ ጊዜ አንዳንድ ተማሪዎች በተቃውሞ  አዳራሹን ለቀው ሲወጡ ሌሎቹ ደግሞ ጀርባቸውን  ወደ መድረኩ አዙረዋል።

በኮሌጁ የምርቃ ስነስርዓት ላይ፣ጆሴፍ ባይደን የመግቢያ ንግግር ሲያደርጉ በነበረበት ወቅት፣አንድ ተመራቂ  የፍልስጤም ባንዴራ በመያዝ ፊቱን ከመድረኩ አዙሮ ታይቷል።

አንዳንድ የኮሌጁ መምህራንና ተማሪዎች፣ የፕሬዚዳንቱ ግብዣ እንዲሰረዝ አስቀድመው ጠይቀው የነበረ ቢሆንም፣ ጥያቄው በኮሌጁ ፕሬዚዳንት ውድቅ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።
ታሪኩ ኃይሉ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW