1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መልዕክተኛ የኢትዮጵያ ጉብኝት

ዓርብ፣ መጋቢት 10 2013

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲወያዩ ክሪስ ኩንስ የተባሉ ሴናተር ለመላክ መወሰናቸውን አስተዳደራቸው አስታውቋል። ሴናተር ክሪስ ኩንስ "ዩናይትድ ስቴትስ እያሽቆለቆለ በመጣው እና የአፍሪካ ቀንድን ሰላም እና መረጋጋት በሚያሰጋው የትግራይ ኹኔታ እጅግ ሥጋት ገብቷታል" ብለዋል

Washington Senat Anhörung Richter für Supreme Court
ምስል፦ picture-alliance/AP Photo/J. Martin

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በትግራይ ጉዳይ ወደ ኢትዮጵያ መልዕክተኛ ሊልኩ ነው

This browser does not support the audio element.

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲወያዩ ክሪስ ኩንስ የተባሉ ሴናተር ለመላክ መወሰናቸው ተሰምቷል። የዋይት ሐውስ የጸጥታ ጉዳይ አማካሪ ጄክ ሱሉቫን ፦ ሴናተሩ በትግራይ ክልል ስላለው ሰብዓዊ ቀውስ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት አሜሪካ ያላትን "ብርቱ ሥጋት" የሚገልጽ መልዕክት ለኢትዮጵያ ያደርሳሉ ብለዋል።

የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪው ጄክ ሱሊቫን ባወጡት መግለጫ ሴናተር ኩንስ በጉዳዩ ላይ ከአፍሪካ ኅብረት መሪዎች ጭምር እንደሚወያዩ ገልጸዋል።

የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የረዥም ጊዜ አጋር የሆኑት ኩንስ በበኩላቸው "ዩናይትድ ስቴትስ እያሽቆለቆለ በመጣው እና የአፍሪካ ቀንድን ሰላም እና መረጋጋት በሚያሰጋው የትግራይ ኹኔታ እጅግ ሥጋት ገብቷታል" ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ትናንት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ቋሚ ተወካዮች ጋር በከባቢ አየር ለውጥ ላይ ውይይት አድርገው ነበር። በውይይቱ ላይ የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ምያንማር፣ ኢትዮጵያ፣ ሊቢያ፣ ሶርያ እና የመንን በመሳሰሉ ቀውሶች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ግፊት ማድረጋቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል። ትናንት በትግራይ ለተቀሰቀሰው ሰብዓዊ ቀውስ 52 ሚሊዮን ዶላር ገደማ አገራቸው እንድምትለግስ ይፋ ባደረጉበት መግለጫቸው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጠንከር ያለ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ "ሰብዓዊው ቀውስ ያለ ፖለቲካዊ መፍትሔ መባባሱን ይቀጥላል" ብለዋል።  ከዚህ ባሻገር ግጭት እንዲቆም፣ በኢትዮጵያ አሉ ያሏቸው የኤርትራ ወታደሮች እንዲወጡም ጠይቀዋል። የባይደን አስተዳደር እኚህን ሴናተር ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ መወሰኑ ምን ይጠቁማል? እሸቴ በቀለ በጉዳዩ ላይ በአሜሪካ የዶይቼ ቬለ ወኪል የሆነውን ታሪኩ ኃይሉን አነጋግሮታል። ታሪኩ ክሪስ ኩንስ ማን ናቸው? የሚለውን በማብራራት ይጀምራል።

ታሪኩ ኃይሉ

እሸቴ በቀለ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW