ፖለቲካሰሜን አሜሪካ
የአምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ኃላፊነት የመልቀቅ ጉዳይ
ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 8 2014
ማስታወቂያ
በአፍሪካ ቀንድ የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ልዑክ ዴቪድ ሳተርፊልድ ሥልጣኑን በያዙ በአጭር ጊዜ ሥልጣን እንደሚለቁ መገለጹ ያልተለመደ ውሳኔ መሆኑን አንድ የቀድሞ የዩናይትድስቴትስ ዲኘሎማት ገለጹ።
በኢትዮጵያና በቡርኪናፋሶ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር ዴቪድ ሺን በተለይ ለዶይቸ ቨለ እንዳሉት፣ ልዩ ልዑኩ ለምን ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ የሚያውቁት ነገር ባይኖርም ዕርምጃው ባልተለመደ ሁኔታ በአጭር ጊዜ የተወሰደ ነው።
በዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የጥናት ማዕከል አትላንቲክ ካውንስል የአፍሪካ ማዕከል አባል አቶ ገብርኤል ንጋቱ በበኩላቸው ልዩ ልዑኩ በሱዳን በሚያደርጉት የሰላም ጥረት ችግር ይግጠማቸው እንጂ ስራ እንደሚለቁ ግን አለመናገራቸውን ገልጸዋል።
ታሪኩ ኃይሉ
እሸቴ በቀለ