1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የአረንጓዴ አሻራ» የችግኝ ተከላ

ዓርብ፣ ሐምሌ 26 2011

ማሂ የአርሴማ ልጅ«ጥንቃቄ ማድረግ እየተቻለ በቸልተኝነት የሆነው ከሆነ ቡኋላ እንደ ቀላል ነገር እንደዚህ ሆነ ማለት እንዴት እጅግ ያሳምማል «ብሔራቸውን መርጠው ያልተወለዱ ወገኖቼ» ነፍሳችሁን በአፀደ ገነት ያሳርፍልን»ብለዋል።የሩቅ ሰው በፌስቡክ «በዞኑ ውስጥ ውጥረት መኖሩ እየታወቀ በቂ የፀጥታ ኃይል ባለማሰማራቱ መንግስትም ተጠያቂ ነው»ይላሉ

Äthiopien Addis Abeba | Premierminister Abiy Ahmed
ምስል DW/Y. Gebregziabher

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

This browser does not support the audio element.

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ በኢትዮጵያ የተካሄደው ብሔራዊ የችግኝ ተከላ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚዎችን ትኩረት ከሳቡት ጉዳዮች መካከል አንዱ ነበር። የሲዳማ ዞን ፖሊስ ከሐምሌ 11፣2011 አንስቶ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች እና ከተሞች በተከሰቱ ግጭቶች ስለሞቱ ስለቆሰሉ እና ስለ ወደመው ንብረት የሰጠው መግለጫም ብዙ አነጋግሯል።የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢ ምርጫዎች መራዘም ልዩ ልዩ አስተያየቶች ተሰጥተውበታል።

ሰኞ ሐምሌ 22፣2011 ዓም «የአረንጓዴ አሻራ» በተባለው ሃገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከማለዳው አንስቶ በተለያዩ አካባቢዎች ችግኞች ተተክለዋል።መንግሥት እንዳስታወቀው።በእለቱ ለመትከል ከታቀደው ችግኝ በላይ ነው የተተከለው።የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የ4 ቢሊዮን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን ገቢራዊ ለማድረግ ብቻቸውንም ሆነ ከእንግዶች ጋር በቤተ መንግሥት እና በሌሎችም አካባቢዎች ችግኝ ሲተክሉ ቆይተዋል።የችግኝ ተከላ ዘመቻው በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከድጋፍ እስከ ትችት ከሙገሳ እስከ ወቀሳ ተፈራርቆበታል። 
«የፊተኞቹም ተክለው ነበር። የሚዲያ ሽፋኑም ችግኝ ነበር።የተደረሰበት ውጤት ግን ከዜና አላለፈም።ሲሉ የቀደመውን ልምድ ያስታወሱት ኪዳኔ አስናቀ «መትከል ግብ አይደለም ማጽደቅ ግን ግብ ነው እንዲህ ያለው የእዩልኝ ችግኝ ተከላ ስለማይበጀን እያጸደቁ ውጤቱን ይንገሩን። የሚል ሃሳብ ሰንዝረዋል።ፍሊሞና በሚል ስም  የትዊተር ተጠቃሚ ችግኝ ተከላን «የኢትዮጵያ መንግሥት ለሽግግሩ ጊዜ ያዘጋጀው ብቸኛ ፍኖተ ካርታ ROAD MAP» ብለውታል።
 ሀና በሚል ስም በትዊትር የተጻፈ አስተያየት«ሰው እየነቀሉ ችግኝ ተከላ ድንጋይ ላይ ውሀ ማፍሰስ ነው ካለ አግባብ ያሰርካቸውን ሰዎች ፍታ አምባገነንነት ለማንም አልበጀ»ይላል የለገሰ ወልደ ሃና አጭር የትዊተር መልዕክት ደግሞ «ሚሊዮን የሀገር ችግር በሚሊዮን ችግኝ ተከላ ወሬ ማስቀየስ» ሲል ሄለን ሀናን ደግሞ «አብያችን ለሚወራው ትኩረት ሳትሰጥ ሥራህን ቀጥል ብለዋል። ሲሉ አስተያየታቸውን በጥያቄ ደምድመዋል።«ይሄ ሰውዬ በማለት የፌስቡክ አስተያየታቸውን የሚጀምሩት እንያት ፀጋዬ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማለታቸው ይመስላል «ይሄ ሰውዬ የአካባቢ ልማት እና ጽዳት ሚኒስቴር ቢሆን ይሻለዋል።»ሲሉ ሰብለ ታዬም ከእንያት ጋር የሚመሳሰል አስተያየት ነው የሰጡት« እባካችሁ ለእዚህ ሰው የስራ ድርሻውን አሳውቁልን» ሲሉ ።በፌስቡክ በጉዳዩ ላይ ለመንግሥት ማሳሰቢያ ለጋዜጠኞች ደግሞ ወቀሳ አቅርበዋል ዳምጠው አመጓዝጎራ ።« በየዓመቱ ችግኞች ይተከላሉ። ግን 3 መቶ እንኳ ፀድቀው አናይም!መንግስት ትኩረት ማድረግ ያለበት ከተተከሉ በኋላ መደረግ ስላለበት እንክብካቤ ነው ዘጋቢዎቹም ተተከሉእንጅ ያልፀቁበትንም ምክንያት ጠይቃችሁ ዘግባችሁ አታውቁም! በማለት። የፎቶና የማስመሰል የገፅታ ግንባታ ፖለቲካው በጣም ተደጋግሞ አሰልቺ ሆኖዋል አሁን የሚያሰፈልገው መሬት የወረደ ወጤታማ ስራ ነው» ይህ ደግሞ የኖህ ናሆ የፌስቡክ መልዕክት ነው። ዎሚሚ ዎ «ሰው እያፈናቀሉ ታሪክ እያፈረሱ ችግኝ ተከላ» በማለት ቅሬታቸውን አስምተዋል። ቢኒያም ጲላጦስም የሰው ዘር እያፈናቀሉ ዛፍ መትከል ምን ዋጋ አለው?ሲሉ ህሊና ዘሩ ደግሞ «ኑሮው ሊያሳብደን ነው እሱ እየዞረ ችግኝ ይተክላል»ሲሉ አማረዋል።ባቲ ባቲ ባቲ «ሠውም ተቃራኒ ሆኖ ያወራል አብይዬም ከመሥራት ወደ ሃላ አላለም ሀሣብህ ተሣክቶ ሀገራችን ሠላም የምትሆንበትን ቀን ያምጣልን ችግኙም ይለምልም ሲሉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ሌላው በዚህ ሳምንት ልዩ ልዩ አስተያየቶችን ያስተናገደው በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል የሲዳማ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥ ምክትል ኮማንደር ዳኛቸው ደምሴ  በሲዳማው ግጭት ስለደረሰው ጉዳት እና ጥፋት  የሰጡት መግለጫ ነው። አዛዡ ለዶቼቬለ በሰጡት መግለጫ የግጭቱ መንስኤ ሐምሌ 11፣2011 በሐዋሳ ከተማ የሲዳማ ብሔር በክልል የመደራጀት ጥያቄን እናውጃለን የሚሉ ወጣቶች ከፀጥታ አካላት ጋር መጋጨታቸው መሆኑን አረጋግጠዋል።በዚሁ መግለጫ በሐዋሳ እና በዞኑ ልዩ ልዩ ልዩ ወረዳዎች እና ከተሞች በተዛመተው ግጭት የ53 ሰዎች ህይወት ማለፉን ቁጥራቸው 54 የሚደርስ መቁሰላቸውን እንዲሁም በርካታ ንብረት መቃጠሉንን እና መወደሙንም ተናግረዋል። በዚህ መግለጫ ላይ ቁጣ ቁጭት እና ስጋት የተንጸባረቀባቸው ልዩ ልዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል። ማሂ የአርሴማ ልጅ በሚል የፌስቡክ ስም  « ጥንቃቄ ማድረግ እየተቻለ በቸልተኝነት የሆነው ከሆነ ቡኋላ እንደ ቀላል ነገር  እንደዚህ ሆነ ማለት እንዴት እጅግ ያሳምማል !!! ካሉ በኋላ «ብሔራቸውን መርጠው ያልተወለዱ ወገኖቼ» ላሏቸው ነፍሳችሁን በአፀደ ገነት ያሳርፍልን»ብለዋል።የሩቅ ሰው በፌስቡክ መንግሥትን ነው የወቀሱት።«በዞኑ ውስጥ ውጥረት መኖሩ እየታወቀ በቂ የፀጥታ ኃይል ባለማሰማራቱ መንግስትም ተጠያቂ ነው ዜጎች በፈለጉበት ቦታ ሰርቶ የመኖር ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተጥሶ ሊገደሉ አይገባም!!!በማለት።ዘደታም በሚል የፌስቡክ ስም «ይህ ሁሉ ሰው ሲሞት የነሱ ስራ ምን ነበር? በሌላው አለም ቢሆን የመጀመሪያው ተጠያቂው የአካባቢው ፖሊስ ነበር::ይላሉ' ሁሉም የክልሉ ህዝብ በከፈለው ግብር በተገዛ ወንበርና መኪና እየተንደላቀቁ በመገናኛ ብዙሀን ወጥተው አንድ ብሄርን ብቻ በመወከል "ሐዋሳ የዕገሌ ካልሆነች በመቃብራችን ነው" የሚሉትን የደቡብ ክልል ቱባ ባለስልጣናት ንግግር እየሰማ የቆየ ስራ አጥ ወጣት ከዚህ የከፋ ነገር ባያደርግ ነው የሚገርመው፡፡የሚሉት ደግሞ ሱሌይማን መሐመድ ናቸው።አጃጆ ኮቴ ተጠያቂው ብሄርተኛው ኢጄቶ መሆን አለበት ምክንያቱም የመጣ ይምጣ ሀምሌ 11 ክልል መሆናችንን እናውጃለን ያለው እሱ ስለሆነ ሙሉ ሃላፊነቱን ይውሰድ ብለዋል።ደረጀ መንገሻ በድሃ ሕዝብ ላብ የተተከለ ፋብሪካ ማቃጠልና መዝረፍ ወንጀል እንጂ የመብት ጥየቃ አይደለም» ።ሲሉ ሞሀ ጃዋ መወገዝ ያለባቸው የሞቱት ወጣቶች ሳይሆን፣ (የተሰጠውን ኻላፍነት ወደ ጎን ትቶ በህዝብ ጥያቄ ላይ የቀለደው)ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው።በማለት መሥሪያ ቤቱን ተጠያቂ አድርገዋል።ትሀታ ኤፍ ወልደ ጊዮርጊስ «ግጭት አልነበረም ፤የተፈፀመው ዘርን ወይንም ቋንቋን መሰረት አድርጎ የተፈፀመ ጥቃት ነው ብለዋል በፌስቡክ  አዲስ አለማየሁ ነፍሰ፡ገዳይ፡በአስቸኳይ፡ለፍርድ፡ይቅረብ ሲል ሚካኤል ልጅ ደግሞ ለሞቱ ነፍስ ይማር።ፈጣሪ ሰላሙን ያውርድ አሜን መልዕክቱን በአጭሩ አስቀምጧል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሳምንቱ አጋማሽ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢ ምርጫዎች ከመጪው ዓመቱ  ሃገር አቀፍ ምርጫ ጋር እንዲካሄዱ መወሰኑም ሲያነጋግር ከርሟል።ደረጀ ላቀ ማርክ «ለምርጫ ጠደፍ ጠደፍ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን?እልቂት ወይስ ተስፋ ስጋት አለኝ»ብለዋል።ሄሊታ ፍቅርሪ የኢትዮጵያ ሕግ ለራሳቸው ሲሆን ይሻሻላል፤ለህብረተሰቡ ሲሆን ደግሞ ለአንድ ብሔር ብለን አናሻሽልም ይላሉ።»በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል።ኦማር ኦሞሳሚ በፌስቡክ«የአዲስ አበባ ህገ-ወጡ አስተዳደር በኢህገ-መንግሥታዊ መንገድ ዛሬ ሥልጣኑ ተራዝሞለታል።የሃገር አቀፍ ምርጫ እና የአአ ምርጫ በአንድ ላይ መደረጉ በመጥፎ አጋጣሚ የሚገኝ መልካም አጋጣሚ ሆኖ አግኝቸዋለሁ።»ብለዋል።

ምስል DW/ Y.Gegziabher
ምስል DW/S. Wogayehu

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW