1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የመጨረሻዎቹ ምስክሮች

ዓርብ፣ ኅዳር 25 2013

በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ዙሪያ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ለተከታታይ ሁለት ቀናት የዐቃቤህግ ምስክሮችን ለመስማት ያስቻለው ችሎት ትናንት ተጠናቋል፡፡በዚህም ዐቃቤ ሕግ ከጠራቸው 13 ምስክሮች ውስጥ ፍርድቤቱ  የአስሩን  ቃል መስማቱ ታውቋል።

Symbolbild Gericht Gesetz Waage und Hammer
ምስል Fotolia/Sebastian Duda

የመጨረሻዎቹ ምስክሮች ቃል ተደመጠ

This browser does not support the audio element.

በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ዙሪያ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ለተከታታይ ሁለት ቀናት የዐቃቤህግ ምስክሮችን ለመስማት ያስቻለው ችሎት ትናንት ተጠናቋል፡፡በዚህም ዐቃቤ ሕግ ከጠራቸው 13 ምስክሮች ውስጥ ፍርድቤቱ  የአስሩን  ቃል መስማቱ ታውቋል።

ፍርድ ቤቱ ጠበቃ ለማቆም አቅም እንደሌላቸው ለገለጹ ሶስት ተከሳሾችና ጠበቃ ለማቆም አቅም ቢኖራትም ሊቆምላት ፈቃደኛ የሆነ ጠበቃ ማጣቷን ለገለጸችው አራተኛ ተከሳሽ መንግስት ተከላካይ ጠበቃ  እንዲቆምላቸው ባዘዘው መሰረት መፈጸሙንም በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተደራጁና ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ለዶይቼ ቬለ አሳውቋል፡፡

ጉዳዩን የሚከታተለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ-ሽብርና ህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ምርመራ ችሎት ብይን ለመስጠትም ለየካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ  ተጨማሪውን ዘገባ አድርሶናል፡፡

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW