የአስመራው ስብሰባ እና የአፍሪቃ ቀንድ ስጋት
ሐሙስ፣ መስከረም 30 2017የምስራቅ አፍሪካው ውጥረት
የምስራቅ አፍሪካ ውስጥ የነገሰው ውጥረት አባባሽ ሁነቶችን እያስተናገደ መስሏል፡፡
ትናንት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ ኤርትራ አስመራ መድረሳቸው እና የግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታ አልሲሲን ጨምሮ ከኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የሶስትዮሽ ውይይት ማድረጋዊ በሰፊው እየተዘገበ ነው፡፡
ይህ ደግሞ የአፍሪካ ቀንድ ላይ ከኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት መሻከር ጋር ተያይዞ በቀጣናው ያንዣበበውን የግጭት ስጋት በሰፊው አባብሶት ተስተውሏል፡፡
“ትናንት እስከ ምሽት አራ ሰዓት ተደዋውለን አውርተናል፡፡ ዛሬ ግን ኔትዎርክ ይሁን ምን በተደጋጋሚ ብደውልም ስልክ አይሰራም” ያሉን አስመራ ከአጎታቸው ጋር ዛሬ በተደጋጋሚ ደውለው ስልክ አለመስራቱን ያረጋገጡን አስተያየት ሰጪ ለዶይቼ ቬለ የገለጹት ነው፡፡
በጎረቤት አገሮች የሚካሄዱ ግጭቶች በኢትዮጵያ የጋረጡት ፈተና
ሌላም አስተያየት ሰጪ የኢትዮ ቴሌኮም መስመር ወደ አስመራ አልሰራ በማለቱ በሳፋሪ ኮም ኢንተርኔት ብቻ መገናኘታቸውን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም ወደ ኤርትራ አገልግሎት ስሰጥ የነበረውን የቴሌኮሚዩኔኬሽን አገልግሎት ስለመቋረጥ አለመቋቋጥ ያለው ነገር የለም፡፡ ወደ ኩባንያው ሃላፊዎች ደውለን ጉዳዩን ለማረጋገጥም ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልሰመረም፡፡ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ጋርም ደውለን ተጨማሪ መረጃዎችን በጉዳዩ ላይ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡
ግብጽን ያንደረደረው ውጥረት በሶማሊያና ኢትዮጵያ መካከል
ከዚህ በፊት ለዓመታት በረራውን ወደ አስመራ ስያደርግ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራውን ሙሉ በሙሉ ማቆሙ በብዙ አነጋግሮ እንደ ነበርም አይዘነጋም፡፡
ከትናንት ጀምሮ ደግሞ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ፣ የግብጽ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታ አልሲሲ እና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አስመራ ውስጥ ተገናኝተው ስለሶሰረትዮች ጥምረቶች ውይይት ማድረጋቸው ተራ የዲፕሎማሲ ምክክር ተደርጎ ብቻ አልታየም፡፡
የግብፅና ኤርትራ ወዳጅነት፤ የደባርቁ ጦርነት፤ የቱርክ የድርድር ጥረት
ዶ/ር የሺጥላ ወንድመነህ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮሌጅ ኦፍ ዴቨሎፕመንት ስቴዲስ ቀጠናዊና ክልላዊ ትምህርት ክፍል መምህር ናቸው፡፡ እንደሳቸው ማብራሪያ ሰሞነኛው የግብጽ የምስራቅ አፍሪካ ልዩ እንቅስቃሴ ረጅም ሂደትን የፈጀና የጂኦ ፖለቲካ ጥቅሟን በቀጣናው ለማስጠበቅ የምታደርገው አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡ “ግብጽ የቀይባህርን በበላይት ለመቆጣጠር በማለም በአፍሪካ ቀንድ ላይ ዘለግ ያለ ፍላጎት አላት፡፡ የአባይ ወንዝ ሌላው የጥቅሟ ማጠንጠኛ አድርጋ ነው የምትመለከተው፡፡ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያኖረችውን የባህር በር ስምምነትን ተከትሎ ከሶማሊያ ጋር የገባችበትን አጣብቂኝና ድህረ ፕሮቶሪያ ስምምነት ከኤርትራ ጋርም የሻከረውን ግንኙነት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም እጇን ለማስገባት የምታደርገው ቅጥያ ነው ሰሞነኛው የሶስትዮሹ ጥምረት” ሲሉ ምልከታቸውን አጋርተውናል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ በረራ አቆመ
ትውልደ ኤርትራዊው የምስራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ አብዱራሃማን ሰኢድ በአስመራ እየተደረገ ያለው የሶስትዮሹ ስምምነት ምናልባትም በቀጣናው ጦርነት ሊያስከትል የሚችል መሆኑ በጉልህ የሚታይ ነው የሚል እምነታቸውን አስረድተዋል፡፡ “ነገሩ ወደ ጦርነት እያመራ ነው የሚመስለው፡፡ ጠንቁ ደግሞ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያኖረችው ስምምነት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከዚህ በፊት የጂኦፖለቲካው ጋር በማያያዝ በአባይ ውሃ እና በቀይ ባህር ጉዳይ ላይ የሚያራምዱት ፖሊሲ ይመስላል፡፡ ይህም ለኢትዮጵያ ጎረቤቶች ስጋትን ያጫረ ይመስላል፡፡ በአባይ ውሃ ላይ ልዩ ክትትል የምታደርገውና ፍላጎትም ያላት ግብጽ ደግሞ በዚህ አጋጣሚ ለመጠቀም እየተንቀሳቀሰች ያለ ነው የሚመስለው፡፡ እናም ሶስቱ አገራት የኢትዮጵያ ምግስት በአባይና ቀይ ባህር ላይ ያለውን ፖሊሲ ለመግታት የሚመክሩ ነው የሚመስለው” ብለዋል፡፡
ግብጽ ባንዳ ሲሉ የጠሯቸውን የውስጥ ኃይሎች በመጠቀም ግጭት እንዲፈጠር እየሰራች ነው
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ኦፍ ዴቨሎፕመንት ስቴዲስ የቀጠናዊና ክልላዊ ተንታኙ ዶ/ር የሺጥላ ወንድመነህ ግን በሶስቱ አጋራት ከኢትዮጵያ ጋር ቀጥተኛ ጦርነት ውስጥ መግባት እምብዛም እርግጠኛ መሆን ይከብዳል ይላሉ፡፡ ከዚያም ይልቅ የእጅ አዙር ጦርነት ምናልባትም ትልቁ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል እንደሆነ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ “በአገራቱ መካከል ቀጥተኛ የሆነ ጦርነት ይከሰታል የሞል እምነት የለኝም፡፡ ምናልባት ወደ ሶማሊያ በሚጫን የጦር መሳሪያ ደንበበር አከባቢ ፍርሃት የመፍጠር እንቅስቃሴ ብደረግ ነው፡፡ ቀጥታ በአገራቱ መካከል ግን መደበኛ ጦርነት ይካሄዳል የሚል እምነት የለኝም” ሲሉም ሃሳባቸውን ቋጭተዋል፡፡
ሥዩም ጌቱ
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ