1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘሙና የተቃዋሚዎች አስተያየት

ሐሙስ፣ መጋቢት 21 2009

በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ የተደነገገዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋን በጥብቅ ተቃወሙ። ፓርቲዎቹ በሰጡት አስተያየት ርምጃዉ «ጠቀሜታ የሌለዉ» «ነፃነትን የሚገድብ» ሲቪል መንግሥት ሃገሪቱን ማስተዳደር አለመቻሉን የሚያሳይ» ሲሉ ተናግረዋል።

Ethiopia State of Emergency Merkel (picture alliance / AP Photo)
ምስል picture-alliance/AP Photo

REAX_Oppositioneller Parteien Ausnahmezustand verlängerung - MP3-Stereo

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስበሰባ የአስቸኳዩ ጊዜ አዋጅ በአራት ወራት እንዲራዘሙ ተቃዋሚዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴአቸዉን ፤ የመናገር ነፃነታቸዉን የሚገፍና በወታደራዊ አስተዳደር ስል እንዳለ ነዉ ሲሉ ለዶቼ ቬለ ዛሬ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስበሰባ የአስቸኳዩ ጊዜ አዋጅ በአራት ወራት እንዲራዘም መወሰኑን ተከትሎ ፤ መንግስት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሃገሪቱ ተረጋግታለች  የሚለዉ ፕሮፖጋንዳ ነዉ ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሽዋስ አሰፋ፤ ትናንት ከመንግስት ጋር በተደረገዉ ቅድመ ድርድር ላይ ፓርቲዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ይነሳ በማለቱ በድርድሩ መባረሩን ገልፀዋል።

የዓረና ትግራይ ለልአላዊነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብረሃ ደስታ በበኩላቸዉ ፤ የአስቸኳይ ጊዜ መራዘሙ ሲቪል መንግሥቱ ሃገሪቱን ማስተዳደር አለመቻሉን ያረጋገጠ ነዉ። የሕዝብን መብት የሚገድበዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጨርሶ መታወጅ አልነበረበትም ያሉት አቶ ሙላቱ ገመቹ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀ መንበር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለአራት ወራት ስለመራዘሙ በሰጡት አስተያየት «ጠቀሜታ የሌለዉ» ሲሉ ተናግረዋል።  

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW