የአሶሳ ከተማ የባምባሲ እና መንጌ ወረዳ ነዋሪዎች ዝግጅት
እሑድ፣ ሰኔ 13 2013
ማስታወቂያ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባምባሲ ወረዳ፣ አሶሳ ከተማና መንጌ ወረዳ ነዋሪዎች በነገው ዕለት ሰኞ ሰኔ 14/2013 ዓ.ም በሚካሄደው 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ከምርጫ በኃላም በክልሉ ዘላቂ ሰላም ይሰፋናል የሚል እምነት እንዳላቸው የተዘጉ መንገዶችም አገልግሎት መስጠት አለባቸው ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ምርጫው ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቅም የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ገልጸዋል፡፡ በምርጫ ቦርድ የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫ ጽ/ቤት መረጃ መሰረትም በነገው ዕለት በአሶሳ ዞን ከ 360ሺ በላይ ዜጎች ለመምረጥ ካርድ ወስደዋል፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ
አዜብ ታደሰ