1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች ያመቻቸው ዕድል

ረቡዕ፣ ሰኔ 30 2013

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች ያመቻቸው ዕድል ከፍቷል። ዩኒቨርሲቲው ከመደበኛ ትምህርት በተጨማሪ የተሻለ ውጤትና ተሰጦኦ ያላቸው ተማሪዎች በተለያዩ መርሀ ግብሮች ዕድል አመቻችቶ እያስተማረ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

Äthiopien Campus der Assosa Universität
ምስል፦ DW/N. Desalegn

«የተሻለ ውጤትና ተሰጥኦ ላላቸው ተማሪዎች መርሀግብር አዘጋጅቷል»

This browser does not support the audio element.

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከመደበኛ ትምህርት በተጨማሪ የተሻለ ውጤትና ተሰጦኦ ያላቸው ተማሪዎች በተለያዩ መርሀ ግብሮች እያስተማረ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ ከክልሉ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን የፈጠራ ችሎታቸውን የሚያጎለብቱበት ትምህርት በያዝነው ዓመት በበጋ ወራት ከ100 በላይ ተማሪዎች ሲያሰተምር ቆይቷል። በቀጣይም የክረምት መርሀ ግብርን ጨምሮ ከ200 በላይ  ተማሪዎችን  ለማስተማር  ዝግጅት እያረገ እንደሚገኝ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሳንይንስ፣ ቴክሎጅና ኢንጅነሪንግ  ማዕከል አስተባባሪ የሆኑት መምህር ጌታቸው ገለታ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። 

 በዚህ ማዕከል  የተመረጡ ተማሪዎችን በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ፣ በስነ ሕይወትና የተለያዩ ትምህርት ዘርፎች አቅማቸውን የሚያጎለብቱበት መሆኑን የማዕከሉ አስተባባሪ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም ሶፍትዌር ያበለጸጉ፣ በድምጽ ብክሌት፣ በማኅበረሰተብ አገልግሎት ሥራ ላይ ጥናት ያደረጉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የዕውቅና ሽማልት ተበርክቶላቸዋል። በማዕከሉ ትምህርት እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎችም በቴክሎጂ የተደገፈ  ትምህርት ችሎታቸው እንዲያዳብሩ እገዛ እንዳደረገላቸው ይናገራሉ።፡

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ2008 ዓ.ም  ሥራ የጀመረው የሳይንስ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጅነሪንግና የሂሳብ ማእከል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ከሚገኙት ሁለተኛ ደረጃ የሚገኙ የተሻለ ተሰጥኦ ያላቸውን በክምረምት መርሀ ግብር እስካሁን ከ1000 በላይ ተማሪዎች ማስተማሩን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ ቴክኖሎጅና ኢንጅሪንግ  ማዕከል አስተባባሪ የሆኑት መምህር ጌታቸው ገለታ  በዘንድሮ ዓመት ከዩኒቨርሲቲው በቅርብ ርቀት የሚገኙ ከአሶሳ ከተማና እና አካባቢው ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ በእረፍት ጊዜያት 120 የሁለተኛ ደረጃ  ተማሪዎች በስነ-ሕይወት፣ በፈጠራ፣ በኬሚስትሪ ፣ በኢንፎርሜን ቴክሎጂ ዘርፍ ትምህቶችን የተከታተሉ ሲሆን በተለያዩ ዘርፎች ውጤታማ ጥናቶች መሥራታቸውን ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው በዚህ የክረምት ወራትም  220 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን  ተቀብሎ ለማስማርም በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል የመጀመሪያውና ብቸኛው ዩኒቨርሲቲ ሲሆን በግብርና ምርምርም የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ የሚደርጉ ሥራዎች ከአሶሳ በ112 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው በማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ እየሠራ እንደሚገኘ ጠቁመዋል። ዩኒቨርሲቲው የመማሪ ማስር ሥራ ከጀመረ ወዲህ በጥር ወር 2013 ዓ.ም ለ7ኛ ጊዜ ተማሪዎችን አስመርቋል።

ነጋሳ ደሳለኝ

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW