የአቡነ ማትያስ ክስና የመንግሥት ተቃውሞ
ሰኞ፣ መጋቢት 12 2014
ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የመንግሥት የፀጥታ አካላት የትግራይ ተወላጅ እሳት ውስጥ ወርውረው መግደላቸውንና ይህም እጅግ እንዳሳዘናቸው በገለጹበት በሰሞኑ ንግግራቸው ላይ የሰጡትን አስተያየት፣ ለአንድ ወገና ያደላና የተሳሳተ ሲል መንግሥት ተቃወመ። ቅዱስ ፓትርያርኩ «ትግራይ ሚዲያ ሀውስ» በተባለው መገናኛ ብዙሀን ባሰሙት ንግግራቸው በ2013 ዓ. ም "ትግሬዎችን ለማጥፋት ፣ የተጀመረው" ያሉት ጦርነት "አሁን በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ተስፋፍቶ በአብዛኛው ቦታ ሁከት ፣ ብጥብጥ ፣ ረሃብና ችግር እየደረሰ ነው" ሲሉ ተናግረው ነበር። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሠ ቱሉ "ፓትርያርኩ ያቀረቡት ክስ ለአንድ ወገን ያደላ፣ በቁጥር የጠቀሱት መረጃም የተሳሳተ እና ሆን ተብሎ መንግሥት ላይ ጫና ለማሳደር የተደረገ ነው።" ብለዋል። መንግሥት ድርጊታቸውን ሕዝብን ለመከፋፈል ሲባል የተደረገ አድርጎ ያየዋልም ብለዋል ሚኒስትሩ። የፓትርያርኩ ንግግር ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በሕዝብ ዘንድ የድጋፍም ፣ የተቃውሞም ሀሳቦች በስፋት እየተንሸራሸሩ ይገኛል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ