1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሕግ እና ፍትሕኢትዮጵያ

የአቪዬሽን ሕግ እና አሠራሮችን ጥሰዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ሰኞ፣ ነሐሴ 20 2016

ባለፈው ሐሙስ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሲቪል አቪዬሽን ሕግና አሠራር ጥሰው "ግርግር እና ወከባ" ፈጥረዋል የተባሉ ስድስት ተጠርጣሪዎች ዛሬ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ
ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ መብረር የነበረበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዞ በአየር ሁኔታ ሲስተጓጎል ስድስቱ ወጣቶች “የበረራ ባለሙያዎችን በማስገደድ በረራውን ለማስቀጠል በፈጠሩት አምባጓሮና ግርግር ወንጀል ተጠርጥረው” በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ የኢትዮጵያ ፌድራል ፖሊስ አስታውቋል። ምስል Kola Sulaimon/AFP/Getty Images

የአቪዬሽን ሕግ እና አሠራሮችን ጥሰዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

This browser does not support the audio element.

ባለፈው ሐሙስ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሲቪል አቪዬሽን ሕግና አሠራር ጥሰው "ግርግር እና ወከባ" ፈጥረዋል የተባሉ ስድስት ተጠርጣሪዎች ዛሬ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበዋል። ተጠርጣሪዎቹ ዛሬ 8 ሰዓት ላይ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት መቅረባቸውን ጥብቅና ከቆሙት ሦስት ጠበቆች አንደኛዋ ጠበቃ ጀሚላ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።

ተጠርጣሪዎቹ የፈጸሙትን ድርጊት በተመለከተ የጠየቅናቸው አንድ የበረራ ባለሙያ ማንኛውም ተጓዥ በበረራ መስተንግዶ ሠራተኞች ከአውሮፕላን እንዲወርድ ሲጠየቅ የደኅንነት ጉዳይ ስለሚሆን "ያለምንም ማመንታት ለጥያቄው ተገዢ መሆን ግዴታ ነው" ብለዋል። ተጠርጣሪዎቹ የሽብር ወንጀል ምርመራ ይደረግባቸዋል ተብሏል። 

የኢትዮጵያ አየር መንገድን በርካታ በረራዎች ያስረዘው የትናንቱ የአየር ሁኔታ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጋዦች የሆኑ ሰዎች የአየር መንገዱን የሲቪል አቪዬሽን ሕግና አሠራር በመጣስ ያልተገባ ግርግር እና ወከባ መፍጠራቸውን በመጥቀስ ተጠርጣሪዎቹ ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን ትናንት አስታውቋል።

ከክረምቱ ወቅት ጋር ተያይዞ በተፈጠረው የአየር ጠባይ መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም በሚል ከበረራ መስተንግዶ ባለሙያዎች የተሰጠን ማሳሰቢያ በመጣስ "በማስገደድ በረራውን ለማስቀጠል በፈጠሩት አምባጓሮ እና ግርግር ወንጀል ተጠርጥረው" ሰዎቹ ስለመያዛቸው ፖሊስ አስታውቋል።

ስድስቱ ወጣቶች “ከፀረ-ሰላም ኃይሎች ተልዕኮ ተቀብለው የተንቀሳቀሱ በመሆናቸው በሽብር ወንጀል” ጭምር መጠርጠራቸውን የኢትዮጵያ ፌድራል ፖሊስ ገልጿል። ምስል Eshete Bekele/DW

የሶማሊያ መንግስት ጥያቄ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዉሳኔ

ይሄው ክስተት በተለይ በአንደኛው ተጠርጣሪ የቲክቶክ መገናኛ ዐውታር በቀጥታ ስርጭት የተላለፈ ሲሆን፣ ያንን ተከትሎ በርካቶች ድርጊቱን በመንቀፍ አስተያየታቸውን ሰጥተውበታል።

ለመሆኑ አውሮፕላን ላይ ለተሳፈረ መንገደኛ ሁሉ ከመነሻ እስከ መድረሻ ድረስ በበረራ መስተንግዶ ሠራተኞች የሚሰጡ ማሳሰቢያዎች፣ መግለጫዎች ወይም ማስጠንቀቂያዎች ምን ያህል ሊከበሩ የሚገባቸው ናቸው ስንል የአቬሽን ባለሙያ የሆኑትን አቶ ዮናታን መንክርን ጠይቀናቸዋል።

"ያለምንም ማወላዳት፣ እና ማመንታት" ቀጥታ የምትተገብረው ነው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። አክለውም የአንድ አውሮፕላን መውደቅ ወይም ለአደጋ ተጋላጭ መሆንንን ተከትሎ ባለድርሻዎች ብዙ የሚሆኑት ለዚህ ነው። ምክንያቱም ድንበር ተሻጋሪ በመሆኑ ነው። መንገደኞች የተለያየ ሀገራት ዜጎች የሚካተቱበት በመሆኑ የደህንነት ሥጋት ሊፈጥር የማይችል ሊሆን የግድ ነው። ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱን አመታዊ የሥራ ክንውን ከሳምንታት በፊት በሰጡት መግለጫ ሲያብራሩ "የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ አሠራሮችን ተከትሎ የሚሠራ መሥሪያ ቤት ነው" ሲሉ ብለው ነበር።ምስል Seyoum Getu/DW

 አየር መንገዱ እስከ 2030 ዓ/ም የሚረከባቸው 125 አዳዲስ አውሮፕላኖች ሊገዛ ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው የአየር መንገዱን አመታዊ የሥራ ክንውን ከሳምንታት በፊት በሰጡት መግለጫ ሲያብራሩ "የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ አሠራሮችን ተከትሎ የሚሠራ መሥሪያ ቤት ነው" ሲሉ መግለጻቸው ይታወሳል። የአቪየሽን ባለሙያው አቶ ዮናታን መንክር እንደሚሉት የአየር መንገዱ ደንበኞች የፈፀሙት ድርጊት በሀገሪቱና ዓለም አቀፍ ሕግጋት ለዳኝነት የሚያቀርባቸው ነው።

በኢትዮጵያ አየር መንገድም ይሁን በሌሎች አየር መንገዶች ለመጓዝ ቲኬት የሚቆርጥ ማንኛውም ተጓዥ ወደሚፈልገው ቦታ እና መዳረሻ ለመጓዝ የአውሮፕላን ቴኬቱን ሲገዛ ከደኅንነት መሣሪያዎች፣ ከሻንጣ እና መሰል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ስምምነቱን የሚገልጽባቸውን ደንቦች እና መመርያዎችን አስቀድሞ ይሞላል።

ሰለሞን ሙጬ
እሸቴ በቀለ
ማንተጋፍቶት ስለሺ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW