1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የአቶ ለማ መገርሳ ስንብትና ቀጣይ እርምጃቸው

ረቡዕ፣ ነሐሴ 13 2012

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ምናልባትም ዘመን ተሻጋሪ አሻራን  ስለማሳረፋቸው በርካቶች የሚመሰክሩላቸው የቀድሞ የመከላከያ ሚንስትር ለመባልም የበቁት አቶ ለማ መገርሳ አሁን ላይ የራሳቸውን መንገድ የለዩ መስለዋል፡፡

Äthiopien Lemma Megersa, Verteidigungsminister
ምስል፦ Prime Minister Office, Addis Ababa

የአቶ ለማ ቀጣይ የፖለቲካ ጉዞ የተለያዩ መላምቶችን እያሰጠ ነው

This browser does not support the audio element.

 

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ምናልባትም ዘመን ተሻጋሪ አሻራን  ስለማሳረፋቸው በርካቶች የሚመሰክሩላቸው የቀድሞ የመከላከያ ሚንስትር ለመባልም የበቁት አቶ ለማ መገርሳ አሁን ላይ የራሳቸውን መንገድ የለዩ መስለዋል፡፡አስቀድሞም በመደመርና በብልጽግና አካሄድ አልተስማማሁም በሚል ለሚዲያ ወጥተው የተናገሩት አቶ ለማ ምናልባትም መርተው እዚህ ደረጃ ላይ በማድረስ የተሳተፉበትን የለውጥ ሂደት ትተው ለመውጣት የባቀቻው ገፊ ምክኒያት ምን ይሆን የሚል ጥያቄ ግን በበርካቶች አዕምሮ ዘንድ በቂ ምላሽን አላገኘም፡፡የፓርቲ ተሳትፎአቸው መቋረጥ ከሳምንት በፊት ሲሰማ በመንግስታዊ ኃላፊነታቸው ይቀጥሉ ይሆናል የሚል ተስፋን ያላሟጠጠ ቢሆንም በትናንትናው እለት በእሳቸው የኃላፊነት ቦታ አዲስ የመከላከያ ሚንስትር የመሾሙ ዜና ይፋ መሆንን ተከትሎ የአቶ ለማ ቀጣይ የፖለቲካ ጉዞ የተለያዩ መላምቶችን እያሰጠ ነው፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቨሌ ያጋሩት የፖለቲካ፣ የጋዜየኝነት እና የህግ  ባለሙያዎች አቶ ለማ መገርሳ ከመንግስታዊ ኃላፊነታቸውም ጭምር መለየታቸው አሁን እርግጥ ቢሆንም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ያላቸው ሚና ግን አሁንም እንደማያበቃ ምልከታቸውን አስቀምጠዋል፡፡አስተያየቶቹን ያሰባሰበው ስዩም ጌቱ ከአዲስ አበባ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል። 


ስዩም ጌቱ 
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW