አቶ ሐብተ ሥላሴ ታፈሰ
እሑድ፣ ነሐሴ 7 2009ማስታወቂያ
ብዙ ሀገር ጎብኚዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲጓዙ ትልቅ አስተዋፅዎ ያበረከቱት አቶ ሐብተ ሥላሴ ታፈሰ ዕሮብ ዕለት በ90 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የአቶ ሐብተ ሥላሴ የኢትዮጵያን «የ13 ወር ፀጋ» የሚለውን የቱሪዝም ማስተዋወቅያ የፈጠሩ እና ለኢትዮጵያ ቱሪዝም እድገት የለፉ ናቸው። ለሚደነቀው አስተዋጾዋቸውም የኢትዮጲያ ቱሪዝም አባት እየተባሉ ይጠራሉ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ በቀብር ስነ-ስርዓታቸው ላይ ተገንቶ አቶ ሐብተ ሥላሴ እንዴት እንደሚታወሱ ዘገባ አጠናቅሮ ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ልደት አበበ