1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተጠርጣሪ ባለሥልጣናት የፍርድ ቤት ውሎ

ዓርብ፣ ኅዳር 7 2011

አቶ ያሬድ ከቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር በመመሳጠር በሽብር የተጠረጠሩ ሰዎች ስውር እሥር ቤቶች እንዲገቡ፣በጨለማ እንዲቆዩ፣ብልታቸው በፒንሳ እንዲሳብ  ፣ብልት ላይ ውሃ የያዘ ፕላስቲክ ማንጠልጠል እና የመሳሰሉ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እንዲፈጸም ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውንም መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤት ገልጿል።

Symbolbild Gericht Gesetz Waage und Hammer
ምስል Fotolia/Sebastian Duda

የአቶ ያሬድ የፍርድ ቤት ውሎ

This browser does not support the audio element.

የቀድሞ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ሃላፊ እና የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ዳይሬክተር ጀነራልአቶ ያሬድ ዘሪሁን በሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በሙስና ወንጀሎች ተጠርጥረው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ፖሊስ አቶ ያሬድ ከቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የቀድሞ ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር በመሳጠር እና በጥቅም በመተሳሰር በርካታ ኢሰብዓዊ ድርጊት መፈጸመቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። ከመካከላቸው በሽብር የተጠረጠሩ ሰዎች ስውር እሥር ቤቶች እንዲገቡ፣በጨለማ እንዲቆዩ፣ብልታቸው በፒንሳ እንዲሳብ  ፣ብልት ላይ ውሃ የያዘ ፕላስቲክ ማንጠልጠል እርቃናቸውን ጉንዳን ማስበላት እና የመሳሰሉ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እንዲፈጸም ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውንም መርማሪ ፖሊስ ገልጿል። አቶ ያሬድ ከአቶ ጌታቸው ጋር በመመሳጠር የተደራጁ ግለሰቦች ወደ ኤርትራ ሄደው ህገ ወጥ ጦር መሣሪያ እንዲያስገቡ በማቀነባበር ህዝብ እንዲሸበር እና በሽብር በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ እንዲሳበብ ማድረግና እንደ ማስረጃ ማቅረብ በሚል ወንጀል እንደጠረጠራቸውም አስታውቋል። በብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የፓወር ፕላንት ሃላፊ ኮሎኔል አሰፋ ዮሐንስም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ዛሬ ፍርድ ከቀረቡት መካከል ይገኙበታል። የእነዚህንን እና የሌሎች ተጠርጣሪዎች የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ተከታትሏል።


ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር  


ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW