1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

የአንቶኒ ብሊንከን የአውሮጳ የጥድፊያ ጉብኝት አንደምታው ምንድን ነው?

ረቡዕ፣ ኅዳር 4 2017

በመጪው ጥር ከኃላፊነታቸው የሚሰናበሩት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር አንቶኒ ብሊንከን በዩክሬን ጉዳይ ከአውሮጳ መሪዎች ጋር ዛሬ ብራስልስ አስቸኳይ ውይይት አድርገዋል ። አንቶኒ ብሊንከን የአውሮጳ መሪዎችን እንዲህ በጥድፊያ ያነጋገሩት በዘንድሮ የአሜሪካ ምርጫ ያሸነፉት ዶናልድ ትራምፕ የፕሬዚደንትነት መንበረ-ሥልጣኑን ከመረከባቸው አስቀድሞ ነው ።

Israel Tel Aviv | Antony Blinken
ምስል Nathan Howard/AP/picture alliance

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር የአውሮጳ አጣዳፊ ጉብኝት አንደምታ

This browser does not support the audio element.

በመጪው ጥር ከኃላፊነታቸው የሚሰናበሩት የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንሥትር አንቶኒ ብሊንከን በዩክሬን ጉዳይ ከአውሮጳ መሪዎች ጋር  ዛሬ ብራስልስ ውስጥ አስቸኳይ ውይይት አድርገዋል ። አንቶኒ ብሊንከን የአውሮጳ መሪዎችን እንዲህ በጥድፊያ ያነጋገሩት በዘንድሮ የአሜሪካ ምርጫ ያሸነፉት ዶናልድ ትራምፕ የፕሬዚደንትነት መንበረ-ሥልጣኑን ከመረከባቸው አስቀድሞ ነው ።

አንቶኒ ብሊንከን ከሩሲያ ወታደሮች ጋር በዩክሬን ድንበር ተሰማርተዋል የተባሉት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ጠንካራ ምላሽ እንደሚሻ ተናግረዋል ። ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉዳዩን ያነሱት ዛሬ በብራስልስ ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል-ኪዳን ድርጅት (NATO) እና ከአውሮጳ ኃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ነው ።

ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሩሲያ ጋር ለምትዋጋው ዩክሬን የጆ ባይደን አስተዳደር በቀሩት ጥቂት ወራት የተቻለውን ያህል ድጋፍ እንደሚያደርግም ማረጋገጫ ሰጥተዋል። አንቶኒ ብሊንከን በአውሮጳ የሚያደርጉትን ጉብኝት በተመለከተ እሸቴ በቀለ በብራስልስ የዶቸ ቨለ ዘጋቢ ገበያው ንጉሤን በስልክ አነጋግሮታል።

እሸቴ በቀለ

ገበያው ንጉሤ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW