የአንድነት አባላት አቶ አንዷለምን መጠየቃቸው
ዓርብ፣ መስከረም 18 2005ማስታወቂያ
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አባላት የእድሜ ልክ እሥራት ተፈርዶባቸው ቃሊቲ እሥር ቤት የሚገኙትን የፓርቲያቸውን ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ አንዷለም አራጌን ለመጀመሪያ ጊዜ መጠየቅ መቻላቸውን አስታወቁ። በትንትናው እለት ወደ ቃሊቲ እስር ቤት የሄዱት የፓርቲው አባላት አቶ አንዷለምን ማነጋገር የቻሉት ጥቂት ከተጉላሉ በኋላ መሆኑንም ተናግረዋል። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ኢንጅነር ዘለቀ ረዲ አቶ አንዷለም የመንፈስ ፅናት እንደሚታይባቸው አስታውቀዋል። አቶ አንዷለም የእድሜ ልክ እሥራት የተፈረደባቸው ባለፈው ሰኔ ነበር። ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ