የአንድ ለአንድ እንግዳችን አቶ ስለሺ ግርማ
ዓርብ፣ መስከረም 30 2018
በኢትዮጵያ የቱሪዝም አገልግሎት መስክ ከአፍላ ወጣትነታቸው ጀምሮ ጉልህ ሚና የነበራቸው ናቸው። ከሀገር አስጎብኚነት እስከ የሚንስትር ዴታነትም ደርሰዋል። ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በነበራቸው የአንድ ለአንድ ቆይታ ከአፍላ የወጣትነት ጊዜያቸው ጀምሮ በቱሪዝም ኢትዮጵያ ውስጥ የነበራቸውን ቆይታ በጥቂቱም ቢሆን አካፍለውናል።
በልጅነታቸው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናትን በማስጎብኘት የጀመረው የቱሪዝም ፍቅር በትምህርታቸው ገፍተው የዩኒቨርሲቲ መምህር እስከ መሆን አድርሷቸዋል። በዚህ ያልተገቱት አቶ ስለሺ የአዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች አገልግለዋል። አሁን የኢፌዲሪ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ዴታ ናቸው ። አቶ ስለሺ ግርማ ።
ወርሃ መስከረም በተለይ በኢትዮጵያ የአዲስ ዓመት መባቻ እንደመሆኑ እና የቱሪዝም ፍሰቱ ከወትሮ ልቆ የሚታይበት ወር እንደመሆኑ መጠን አቶ ስለሺ ስለአዲሱ የኢትዮጵያውያን ዓመት አቀባበል እና የመስከረም ወር እንዴት እንዳለፈም አጫውተውናል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢትዮጵያን ገጽታ ለማስተዋወቅ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ፣ የዲጅታል ዘመን የቱሪዝም ኢትዮጵያ መስህብን ከቀደመው ዘመን ጋር እያነጻጸሩ አውግተውናል።
የጸጥታ ችግር በኢትዮጵያ ያስከተለው መስተጓጎልበቱሪዝም መስክ ላይ ምን ችግር ፈጥሮ ይሆን ? የሚለውን ጨምሮ የኢትዮጵያ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች ደረጃ ፣ አገልግሎት እና የዋጋ ፍትሃዊነት በቱሪዝም ላይ የሚኢሳድረው ጫና ካለ እና የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሚና እና በቅርቡ ወደ አውሮጳ የተጓዙት የሉሲ እና ሰላም ቅሪተ አካላት ለኢትዮጵያ አዲስ የሚያመጡት ገጸ በረከት ካለ ተብለው ለተጠየቁት ሚንስትር ዴታው መልስ ሰጥተዋል።
ታምራት ዲንሳ
ጸሐይ ጫኔ