1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የአንድ ለአንድ እንግዳ ወ/ሮ ራኬብ መሰለ

ዓርብ፣ መጋቢት 26 2017

የአንድ ለአንድ እንግዳችን በተለይ የሕጻናት፤ የሴቶች እና የጾታ ሰብዓዊ መብቶች አጠባበቅ ከፍተኛ ባለሙያ ናቸው። ወ/ሮ ራኬብ መሰለ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሲሆኑ አሁንም የሥራ ጊዜያቸው እንዳላለቀ ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ራኬብ መሰለ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር
ወ/ሮ ራኬብ መሰለ የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ባለሙያ ፎቶ ከማኅደርምስል፦ Solomon Muchie/DW

የአንድ ለአንድ እንግዳ ወ/ሮ ራኬብ መሰለ

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ራኬብ መሰለ ቀደም ባሉት ዓመታት ሕጻናት አድን በተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅት በእስያ፣ ምዕራብ እና ማዕከላዊ አፍሪቃ ውስጥ ባሉ ከ16 የሚበልጡ ሃገራት በልጆችን መብት አማካሪነት አገልግለዋል። በዚሁ ዘርፍ የአቅም ግንባታ ሥራዎችንም ሢሠሩ ቆይተዋል። ደቡብ አፍሪቃ በፕሪቶሪያ ዩኒቨርሲቲ ግሎባል ካምፓስ አፍሪቃ ተቋም በሰብአዊ መብቶች እና በአፍሪቃ ዴሞክራሲዊነት መርኀግብር ከመጀመሪያዎቹ ተመራቂዎች አንዷ ናቸው። እንግዳችን ወ/ሮ ራኬብ መሰለ ሰኔ 18 ቀን 2013 ዓ,ም በምክር ቤት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽን ሆነው ተሹመዋል። ካለፈው ዓመት ሐምሌ አንስቶ እስከ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ,ም ድረስም ኢሰመኮን ሲመሩ ቆይተው በሌላ ኃላፊ ተተክተዋል።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW