1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአንጋፋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይለማሪያም የ30ኛ ዓመት ህልፍተ ህይወት መታሰቢያ ተካሔደ

እሑድ፣ መስከረም 12 2017

ጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይለማርያም በኢትዮጵያ ራዲዮ እና ቴሌቭዥን በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገለ የዶይቼ ቬለው ነጋሽ መሐመድን ጨምሮ አንጋፋ ባለሙያዎች በክብር የሚያስታውሱት ባለሙያ ነበር። በዜና አጻጻፍ እና አቀራረብ የተለየ ክህሎት እንደነበረው የሚነገርለት ጌታቸው ጋዜጠኞች የመስክ ዘገባ እንዲሰሩ በማድረግ ላቅ ያለ አስተዋጽዖ አርክቷል።

የጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይለማርያም መታሰቢያ መርሐ ግብር
ጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይለማርያም በኢትዮጵያ ራዲዮ እና ቴሌቭዥን በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገለ የዶይቼ ቬለው ነጋሽ መሐመድን ጨምሮ አንጋፋ ባለሙያዎች በክብር የሚያስታውሱት ባለሙያ ነበር።ምስል Hanna Demissie/DW

የአንጋፋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይለማሪያም የ30ኛ ዓመት ህልፍተ ህይወት መታሰቢያ ተካሔደ

This browser does not support the audio element.

በወምዘክር መፀሀፍት ቤት አዲስ አበባ በተካሄደው የጋዜጠኛው ዝክረ ህይወት መታሰቢያ  ላይ የስራ ባልደረቦቹና ቤተሰቦቹ  ተገኝተዋል አንጋፋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይለማርያም፣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ከሪፖርተትነት እስከ ፕሮግራም ክፍል ሀላፊ በመሆን አአልግሎዋል።

ጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይለማሪያም ዛሬም ድረስ ስሙ በሙያው ዘርፍ የሚታወስ ሲሆን በሙያው ከ22 ዓመታት በላይ ያገለገለ እውቅ ጋዜጠኛ ነበር። 

አንጋፋው ጋዜጠኛ ተክሌ የኋላ ሲታወስ

የሙያው አፍቃሪዎች እና በህዝብ ዘንድ እስካሁን ስሙ ያልተዘነጋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ሀይለማሪያም በተለይም በዜና አቀራረቡ  ለብዙዎች አርአያ ነበር  ይህ ተወዳጅ ጋዜጠኛ 1938 ተወልዶ 1987 በ49 አመቱ ይህወቱ አልፏል።

ጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይለማሪያምን የዘጋቢ ፊልም ባለሞያ ከመሆኑም ባሻገር “አለም እንደምን ሰነበተች?” በሚል የሚያዘጋጀው ፕሮግራም የሚታዋቅበት ስራዎቹ ናቸው።

ይህን ብርቱ ጋዜጠኛ የሚያውቁት ጌታቸው ሙያውን አክባሪ እና በዘርፍ አዳዲስ ነገርን ለመጀመር  ደፉር ነበር ሲሉ DW ገልፀዋል።                        

የአንጋፋው ጋዜጠኛ ፍቅሩ ኪዳኔ የቀብር ስነስረዓት ተፈጸመ

ጋዜጠኛ ጌታቸው ኃይለማርያም በህይወት ሳለ በርካቶችን በሙያ አርአያ በሆኖ በስጋ ደግሞ ሁለት ልጆችን አፍርቷል። በወቅቱ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ቢያገለግልም የሞቱ ዜና በጣቢያው አለመነገሩ በወቅቱ አነጋጋሪ ነበር። የመታሰቢያ ስነስርዓቱን ያከናወነው ተወዳጅ ሚድያና ኮሚዩኒኬሽንስ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ሐና ደምሴ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW