1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአንጋፋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ደስታ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

ዓርብ፣ ጥር 14 2013

ከ1960 ዎቹ ጀምሮ ለረጅም ዓመታት በኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን፣ በኋላም በጀርመን ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ዶይቼ ቬለ የአማርኛው አገልግሎት ያገለገለው አንጋፋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ደስታ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፀመ።

Äthiopien Addis Abeba | Beerdigung Getachew Desta, DW-Mitarbeiter
ምስል DW

ግብዓተ መሬቱ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናወነ

This browser does not support the audio element.

ከ1960 ዎቹ ጀምሮ ለረጅም ዓመታት በኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን፣ በኋላም በጀርመን ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ዶይቼ ቬለ የአማርኛው አገልግሎት ያገለገለው አንጋፋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ደስታ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፀመ። አንጋፋው ጋዜጠኛ ጌታቸው ደስታ ከጋዜጠኝነት ሞያው ባሻገር በተለያዩ በጎ ሥራዎች ላይም ተሳታፊ ነበር። በተወለደ በ86 ዓመቱ ለህክምና በቆየበት ጀርመን ሀገር ከዚህ ዓለም የተለየው ጋዜጠኛ ጌታቸው አስክሬኑ ወደ ሀገሩ የተመለሰው ትናንት ጥዋት ነበር። የሁለት ልጆችና እንደ ልጆቹ አድርጎ ያሳደጋቸው አምስት ልጆች አባት የነበረው ጋዜጠኛ ጌታቸው ደስታ በኢትዮጵያ ሬድዮ የአድማጮች የሙዚቃ ምርጫንና በቴሌቪዥን የሕብረት ትርዒትን በመምራት ተወዳጅነትን ያተረፈ እንደነበር በሕይወት ታሪኩ ላይ ተገልጿል።
ሰሎሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW