1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉጳ ሕብረት ሚንስትሮች የሰብአዊ ፋታ ጥያቄ ለጋዛ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 4 2016

ሚኒስትሮቹ ቀደም ሲል በጋዛ የሰባዊ እርዳታ ለማድረስ በቀረበው ጥሪ የነበረውን አለመግባባት በማስወገድ በአሁኑ ወቅት አሁኑኑ የሰብአዊ ፋታዎች (Humanitarian pauses) እንዲደረጉ በአንድነት ጥሪ ያቀረቡ መሆኑን የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሀላፊና የስብሰብው መሪ ሚስተር ጆሴፕ ቦርየል አስታውቀዋል።

ብራልስ-ቤልጂግ በተደረገዉ ስብሰባ ሚንስትሮቹ ጋዛ ዉስጥ ሰብአዊ ፋታ እንዲደረግ ወስነዋል
የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት የሚንስትሮች ስብሰባ ምስል Frederic Sierakowski/European Union

የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ለጋዛ ሰብአዊ ፋታ እንዲደረግ ጠየቁ

This browser does not support the audio element.

 

የእስራኤል ጦር ለሚያወድማት የጋዛ ሕዝብ ርዳታ ይደርስ ዘንድ ሰብአዊ ፋታ እንዲደረግ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በድጋሚ ጠየቁ።ጋዛን ከማዉደም ባለፍ ዙሪያ ገባዉን የከበበችዉ እስራኤል ለፍልስጤማዉያኑ ምግብ፣ዉኃ፣ መድሐኒትና ነዳጅ እንዲደርስ አግዳለች።የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ጥያቄቸዉ በእስራኤል ተቀባይነት እንዲያገኝ ያስቀመጡት ሁኔታ ግን የለም።ትናንት ብራስልስ የተሰበሰቡት የ27ቱ ሐገራት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ለዩክሬን መንግስት የሚሰጡት ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉም አስታዉቀዋል።

የሰባዊ ፋታዎች 

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት እዚህ ብራስልስ ባደረጉት ስብሰብ  የጋዛ ሰርጥንና ዩክሬንን ዋና  አጀንዳዎቻቸው አድርገው በመወያየት ውሳኔዎችን አሳልፈዋል። ሚኒስትሮቹ ቀደም ሲል በጋዛ የሰባዊ እርዳታ ለማድረስ በቀረበው ጥሪ የነበረውን አለመግባባት  በማስወገድ በአሁኑ ወቅት አሁኑኑ የሰብአዊ ፋታዎች (Humanitarian pauses) እንዲደረጉ በአንድነት ጥሪ ያቀረቡ መሆኑን  የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሀላፊና የስብሰብው መሪ ሚስተር ጆሴፕ ቦርየል አስታውቀዋል። “ 27ቱ  ሚኒስትሮች በአንድነት አሁኑኑ የሰባዊ ፋታዎች እንዲኖሩና በጋዛ በክፋ ችግር ውስጥ ላሉት እርዳታ እንዲደርስ እንዲደረግ ያለምንም ልዩነት ጥሪ ያቀረቡ መሆኑን በመግለጽ በዚህ ጉዳይ ልዩነት የሌለ መሆኑን አረጋግጠዋል።  

የ27ቱ የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ምስል Frederic Sierakowski/European Union

 

ሚኒስትርቹ  ወደ ጋዛ በምድርም ይሁን በባህር  ተጨማሪ እርዳታ ስለሚገባበት ሁኔታ፤ ሁሉም  በሀማስ የተያዙ ታጋቾች ያለምንም ቅድመ ሁኒታ ባስቸኳይ እንዲለቀቁና ቀይ መስቀልም እንዲጎበኛቸው እንዲደረግ አጥብቀው ያሳሰቡ መሆኑም ታውቁል። በተጨማሪም ግጭት ጦርነቱ የበለጠ እንዳያድግና እንዳይስፋፋ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በማመን፤ ህብረቱ ከአካባቢው አገሮችና ሌሎች አጋሮች ጋር በጋራና በቅርበት ትኩረት ሰቶ መሰራት እዳለበትም ሚኒስትሮቹ  እንዳመኑበት ተገልጿል።
 

ጋዛ በድህረ ጦርነት

ከወር በላይ የዘለቀውና እስካሁን ከ1400 በላይ እስራኤላውያንና ከ11 ሺ በላይ ፍልስጤማውያንን ለሞት የዳረገው  የሀማስ እስራኤል ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ፤ በተለይ በዚህ ስብሰባ ከጦርነቱ ማግስት ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር መደረግ ባለባቸው ጉዳዮች ላይ በሰፈው ውይይት ተደርጓል ተብሏል። የውጭ ጉዳይ ሀላፊው በሥፓኒሽ ቋንቋ  በሰጡት ጋዜጣዊ መገለጫቸው፤ በጦርነቱና በተፈጠረው ቀውስ የበርካታ  ፍልስጤሞችና እስራኤልውያንም ህይወት ማለፉ፤ ያለማቀፉን  ማህብረሰብ ድክመትና የሞራል ውድቀት የሚያሳይ ነው በማለት፤ እስካሁን ለችግሩ መፍትሄ ለማስገኘት አለመቻሉ ትልቅ ድክመት መሆኑን አንስተዋል። ሚስተር ቦርየል አሁን የተፈጠረው ሁኔታ ሁለቱ ህዝቦች ጎን ለጎን የሚኖሩበትን እድል ለመፍጠር የሚያስችል መሆን ይኖርበታል በማለትም፤  ለሁለት ህዝቦችና ሁለት አገሮች የመፍትሄ ሀሳብ ከልብ መስራት የሚያስፈልግ መሆኑን  አስገንዝበዋል።

ከጋዛ ዉድመት አንዱምስል Mohammed Abed/AFP/Getty Images

 

ሚስተር ቦርየል በዚህ ሳምንት የእስራኤልና  የፍልስጤም ግዝቶችን የሚጎበኙ መሆኑንም የገለጹ ሲሆን፤ በድሀረ ጦርነቷ ጋዛ  መሆን ያለባቸውና መሆን የሌለባቸው ያሉዋቸውንና ለሚኒስትሮቹ አቅርበው ድጋፍ የተቸራቸውን አዲስ ሀሳቦች ይፋ ድርገዋል።   እንደውጭ ጉዳይ ህላፊው አስተየየት መሆን የማይኖርባቸው፤  የእስራኤል ጦር ጋዛን በቋሚነት መያዝ አይኖርበትም፤  ፍልስጤሞች በህይል ሊፈናቀሉ አይገባም፤ ጋዛ ከፍልስጤም ግዛት መነጠል የለባትም የሚሉት ሲሆኑ መሆን ይኖርባቸዋል ያሉዋቸው ደግሞ  የፍልስጤም አስተዳደር ጋዛን መጠቅለል  ይኖርበታል፤ አንድ የፍልስጤም አስተዳር ሊኖር ይገባል፤ ይህ አስተዳደርም በተባበሩት መንግስት የጽጥታው ምክርቤት የታወቀው  መሆን አለበት የሚሉት እንደሆኑ ተገልጿል። ይሁን እንጂ እስራኤል ጋዛን ከጦርነቱ በኋላ የምትለቅ ስለመሆኗ እስካሁን በግልጽ ያለችው የለም፤ ጦርነቱም መቼና እንዴት እንደሚያበቃ እንደማይታወቅ ነው የሚነገረው። ያም ሆኖ ከጦርነቱ ወዲህ ወደ አካባቢው ያልዘለቁት ሚስተር ቦርየል እነዚህን የድህረ ጦርነት የሰላም ሀሳቦች ይዘው ከእስራኤል፤ የፍልስጠኤምና የአካባቢ አገሮች ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ነው የሚጠበቀው።

የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬልምስል European Union

ዩክሬን አሁንም የህብረቱ ዋና አጀንዳ

ሚስተር ቦርየል  የመከክለኛው ምስራቅ ችግርና የጋዛ ቀውስ ሚኒስትሮቹን ዩክሬንን እንዳላስረሳቸው አስታወሰው፤ ዩክሬን አሁንም የህብረቱ አይነተኛ አጀንዳ መሆኗንም አስታውቀዋል፤ “  ዩክሬን አሁንም የህብረቱ ዋና አጀንዳ እንደሆነች ናት። ሚስትር ፑቲን ክረምትንና እረሀብን እንደጦር መሳሪያ ሊጠቀሙበት እንደሚያስቡ እናውቃለን” በማለት ለዩክሬን የሚስጠው የመሳሪያ፤ የገንዘብና የስልጠና   ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል  አስታወቀዋል።

ገበያው ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ


 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW