1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረት ዉሳኔና ሶማሊያ

ዓርብ፣ መጋቢት 14 2004

የሕብረቱ አባል ሐገራት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ዛሬ ባሳለፋት ዉሳኔ መሠረት ግን ጦሩ መሬትም የሚገኙ የባሕር ወንበዴዎችን እየተከታተለ ያጠቃል። መሳሪያዎቻቸዉንም ይመታል።ሚንስትሮቹ ለጦራቸዉ ተልዕኮ ማፅፈፀሚያ ተጨማሪ ገንዘብ መድበዋልም

Ein Soldat der Spezialisierten Einsatzkraefte der Marine (SEKM) geht waehrend einer Anlandungsuebung in der Naehe von Eckernfoerde im Wasser (Foto vom 26.09.07). / Eingestellt von wa (Foto: dapd)
የአታላንታ ባልደረባምስል dapd


የሶማሊያ የባሕር ላይ ወንበዴዎችን ለመዉጋት የዘመተዉ የአዉሮጳ ሕብረት የባሕር ጦር የብስ ላይ የሚገኙ የባሕር ወንበዴዎችንና መሳሪያቸዉን እንዲመታ ሕብረቱ ወሰነ።አታላንታ የተሰኘዉ የአዉሮጳ ባሕር ሐይል የእስካሁን ተልዕኮ የወንበዴዎቹን ጥቃት ባሕር ላይ መከላከል ነበር።የሕብረቱ አባል ሐገራት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ዛሬ ባሳለፋት ዉሳኔ መሠረት ግን ጦሩ መሬትም የሚገኙ የባሕር ወንበዴዎችን እየተከታተለ ያጠቃል። መሳሪያዎቻቸዉንም ይመታል።ሚንስትሮቹ ለጦራቸዉ ተልዕኮ ማፅፈፀሚያ ተጨማሪ ገንዘብ መድበዋልም።የፀረ-ባሕር ወንበዴዎች ዉጊያዉ ከባሕር አልፎ በየብስም እንዲደረግ ቢወሰንም ሕብረቱ እግረኛ ሠራዊት አያዘምትም።የሚንስትሮቹን ስብሰባ ዉሳኔ የተከታተለዉ የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ እንደሚለዉ ግን የሕብረቱ ባሕር ሐይል ጦር የኢትዮጵያን ጨምሮ ሶማሊያ ከሰፈረዉ የተለያዩ ሐገራት ሠራዊት ተልዕኮ ጋር ሳይቀናጅ አይቀርም።ገበያዉን በስልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW