1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረት የስደተኞች ዕቅድ

ረቡዕ፣ ጳጉሜን 4 2007

ሕብረቱ ለስደት ምክንያት የሆኑ ችግሮችን ለማቃለል የረጅም ጊዜ ዕቅድ እንደሚያስፈልገዉ ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።በተለይ አፍሪቃ ዉስጥ የሚታዩ ግጭቶችን ለማቃለል ኮሚሽኑ 1,8 ቢሊዮን ዩሮ ለመመደብ አቅዷል

ምስል Reuters/V. Kessler

[No title]

This browser does not support the audio element.

የአዉሮጳ ሕብረት ወደ አሐጉሪቱ በብዛት የሚገቡ ሥደተኞችን አባል ሐገራት ተከፋፍለዉ የሚያስተናግዱበትን ዕቅድ ዛሬ ይፋ አደረገ።የሕብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝደንት ዦን ክላዉድ ዩንከር ዛሬ ለሕብረቱ ምክር ቤት ባቀረቡት ዕቅድ መሠረት እስካሁን ድረስ ግሪክ፤ ኢጣሊያና ሐንጋሪ የሚገኙ 120 ሺሕ ተጨማሪ ስደተኞችን ሌሎች ሐገራት በኮታ ይከፋፈሏቸዋል።ሕብረቱ ለስደት ምክንያት የሆኑ ችግሮችን ለማቃለል የረጅም ጊዜ ዕቅድ እንደሚያስፈልገዉ ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።በተለይ አፍሪቃ ዉስጥ የሚታዩ ግጭቶችን ለማቃለል ኮሚሽኑ 1,8 ቢሊዮን ዩሮ ለመመደብ አቅዷል።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW