1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካየመካከለኛው ምሥራቅ

የአዉሮጳ ሕብረት ጉባኤ በእስራኤል-ሐማስ ጦርነት ላይ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 7 2016

መሪዎቹ በሚወያዩበት መሐል አል አሕሊ አል አረብ የተባለዉ የጋዛ ጥንታዊ ሆስፒታል በቦምብ ወይም ሚሳዬል ተመትቶ አምስት መቶ ሕሙማን፣ የሕክምና ባለሙያዎችና ተፈናቃዮች መገደላቸዉ የጉባኤዉን መንፈስ አዉኮታል።

የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት መሪዎች ጉባኤ
የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት መሪዎችና የሕብረቱ ኮሚሽን ባለስልጣናትምስል Albania Prime Minister Press Office

የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት መሪዎች ትናንት በርቀት (Online) ባደረጉት ጉባኤ እየከፋ ስለመጣዉ የእስራኤልና የሐማስ ጦርነት ተነጋግረዋል።የሕብረቱ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሻርልስ ሚሼል አስቸኳይ ጉባኤዉን የጠሩት የአባል ሐገራትና የኮሚሽኑ መሪዎች በጦርነቱና ዉጤቱ ላይ የጋራ አቋም እንዲይዙ ለማድረግ ነዉ ተብሏል።መሪዎቹ በሚወያዩበት መሐል አል አሕሊ አል አረብ የተባለዉ የጋዛጥንታዊ ሆስፒታል በቦምብ ወይም ሚሳዬል ተመትቶ አምስት መቶ ሕሙማን፣ የሕክምና ባለሙያዎችና ተፈናቃዮች መገደላቸዉ የጉባኤዉን መንፈስ አዉኮታል። ይሁንና መሪዎቹ በጉባኤዉ ማብቂያ ላይ አራት ነጥቦች የያዘ የአቋም መግለጫ አዉጥተዋል።

ገበያዉ ንጉሤን 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ


 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW