1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ኅብረትና የሩስያ ዉዝግብ

ማክሰኞ፣ መስከረም 5 2013

በቤላሩስ ፕሬዚዳንት ሉካሼንኮ ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቀዉ ተቃዉሞ ከተቀሰቀሰ ወዲህ እና የፑቲን ዋንኛ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ መመረዛቸዉ ከታወቀ በኋላ በሩስያና በአዉሮጳ ኅብረት መካከል ያለዉ ግንኙነት የሻከረ ይመስላል። በቤላሩስ በበኩልዋ በቤላሩስ ለተከሰተዉ ቀዉስ አዉሮጳዉያንና ሌሎች ጣልቃ ገብነት አስተዋፅኦ እያደረገ ነዉ ስትል ታማርራለች።

Weißrussland | Proteste in Minsk
ምስል Reuters/Tut.By

ሩስያ ናቫልኒ በመመረዙ የቀረበባትን ክስ አትቀበልም

This browser does not support the audio element.

 

የሩስያና አዉሮጳ ግንኙነት በተለይ በቤላ ሩስ ከተቀሰተዉ የፖለቲካ ቀዉስ እና ከታዋቂዉ ፖለቲከኛ አሌክሴይ ናቫልኒ መመረዝ በኋላ  ከፍተና ችግር ዉስጥ ገብቶአል። አዉሮጳ ሞስኮን ቤላሩስያዉያን ምርጫ አጭበርብረዋል የሰብዓዊ መብት ጥሰዋል የሚልዋቸዉን ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ በመደገፍ እና የፕሬዚዳንት ፑቲንን መንግሥት በመተቸት የሚታወቀዉን አሌክሴይ ናቫልኒን በመመረዝ ይከሳል። ሩስያ ግን የቀረበባትን ክስ አትቀበልም። እንደዉም በቤላሩስ ለተከሰተዉ ቀዉስ አዉሮጳዉያን እና ሌሎች ጣልቃ ገብነት አስተዋፅኦ እያደረገ ነዉ ስትል ታማርራለች። የናቫልኒ መመረዝ ጉዳይም መረጃ የማይቀርበት ሞስኮን የማጠልሸት ተግባር ነዉ ስትል ትከራከራለች። እያደገ እና እየሰፋ የሄደዉ የቤላሩስያዉያን ፀረ ሉካሼንኮ ተቃዉሞ እና የናቫልኒ የሕክምና ዉጤት ይህን የሁለቱን ወገኖች ዉዝግብ እና አለመግባባት እየሠፋዉ እና እያከረረዉ የሚሄድ እንጂ የሚያላላዉ ብሎም የሚያለዝበዉ አልሆነም።

ሙሉ መሰናዶዉን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ ! 

 

ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW