1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የአዉሮጳ ኅብረት መሪዎች ለዩክሬይን 105 ቢሊዮን ዶላር ለማበደር ተስማሙ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 10 2018

የአውሮጳ ህብረት መሪዎች ለዩክሬን የ 105 ቢሊየን ዶላር ወይም 90 ቢሊዮን ዩሮ ለማበደር ዛሬ አርብ ስምምነት ላይ ደረሱ። ይህ ብድር ዩክሬይን ያለባትን የበጀት እጥረቶች ይሸፍናል ተብሏል። ይሁንና መሪዎቹ በአዉሮጳ ሃገራት የተያዙ የሩስያ ቱጃሮች ንብረቶችን ለዩክሪይን ይዋል በሚለዉ ላይ አልተስማሙም።

የአዉሮጳ ኅብረት ሃገራት መሪዎች ለዩክሬይን ብድር ለመስጠት ተስማሙ
የአዉሮጳ ኅብረት ሃገራት መሪዎች ለዩክሬይን ብድር ለመስጠት ተስማሙ ምስል፦ Michael Kappeler/dpa/picture alliance

የአዉሮጳ ኅብረት መሪዎች ለዩክሬይን 105 ቢሊዮን ዶላር ለማበደር ተስማሙ

This browser does not support the audio element.

የአዉሮጳ ኅብረት መሪዎች ለዩክሬይን 105 ቢሊዮን ዶላር ለማበደር ተስማሙ

የአውሮጳ ህብረት መሪዎች ለዩክሬን የ 105 ቢሊየን ዶላር ወይም  90 ቢሊዮን ዩሮ ለማበደር ዛሬ አርብ ስምምነት ላይ ደረሱ። ይህ ብድር ዩክሬይን ያለባትን  የበጀት እጥረቶች ይሸፍናል ተብሏል። ይሁንና መሪዎቹ በአዉሮጳ ሃገራት የተያዙ የሩስያ ቱጃሮች ንብረቶችን ለዩክሪይን ይዋል በሚለዉ ላይ አልተስማሙም። በ 2025 የአዉሮጳ ሃገራት መሪዎች ጉባኤ ማጠቃለየዉ ምን ሆነ? በአዉሮጳ ኅብረት መቀመጫ በሆነዉ በብረስልስ የሚገኘዉን ወኪላችንን በጉዳዩ ላይ አነጋግረነዋል። 

የአውሮጳ ህብረት መሪዎች ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ለዩክሬን ወታደራዊእና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቷን ማሟያ የሚዉል ከወለድ ነፃ ብድር ለመስጠት ተስማምተዋል። ይህን ይፋ ያደረጉት የአውሮጳ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አንቶኒዮ ኮስታ ናቸዉ። እንደ ኮስታ ፤ መሪዎቹ በአዉሮጳ ሃገራት የተያዙ የሩሲያ ንብረቶችን ከመጠቀም ይልቅ ዩክሬን ሩሲያን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ጥሪ ገንዘብን ለመበደር ወስነዋል ሲሉም የአዉሮጳ ሃገራት ዲፕሎማቶች መግለጻቸዉ ተዘግቧል።

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የኪዬቭን መከላከያ "በእርግጥ ያጠናክራል" ሲሉ የዩክሬንን የበጀት እጥረት ለማጠናከር ለአውሮጳ ህብረት ብድር ለመስጠት መስማማቱን አመስግነዋል።

"ይህ የእኛን ኃይል በእውነት የሚያጠናክር ጉልህ ድጋፍ ነው" ሲሉም ዜሌንስኪ በ X ገጻቸዉ ላይ ጽፈዋል። "የሩሲያ ንብረቶች እንዳይንቀሳቀሱ መደረጉ እና ዩክሬን ለሚቀጥሉት ዓመታት የፋይናንስ ደህንነት ዋስትና ማግኘቷ አስፈላጊ ነው" ሲሉም አክለዋል።

ከዚህ ቀደም ሲል የአውሮጳ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አንቶኒዮ ኮስታ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ ይፋ እንዳደረጉት ደግሞ፤ "እኛ በስምምነታችን ፀንተናል።  ለመጭዉ 2026-27 ዓመት ለዩክሬይን ብድር ለመስጠት ተስማምተናል ። ለዩክሬን የ 90 ቢሊዮን ዩሮ [105.5 ቢሊዮን ዶላር] ድጋፍ ለመስጠት የተደረገው ውሳኔ ጸድቋል።"

ዛሬ አርብ በወጣዉ የጽሑፍ ስምምነት መረጃ መሰረት፤ ዩክሬንን በፋይናንስ መርዳት የማይፈልጉት የሃንጋሪ, ስሎቫኪያ እና ቼክ ሪፐብሊክ ብድር ለመስጠት በሚደረገዉ የገንዘብ በዋጮ ላይ ግዴታ የለባቸዉም።

ገበያዉ ንጉሴ / አዜብ ታደሰ

ሸዋዩ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW